በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የማይክሮሶፍት ኢሜል መገልገልያን አልጠለፍኩም አለች


ቻይና ማይክሮሶፍት ኤክስቼንጅ በተባለው ትልቁ ዓለም አቀፍ የኢሜል ልውውጥ መገልገለያ መረብ ላይ ተፈጽሟል ከተባለው የሳይበር ጥቃት በስተጀርባ አለችበት መባሉን አስተባብላለች፡፡ በዚህ ሳምንት፣ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አባል አገራት ኔቶ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ እና ኒውዘላንድ ከዩናይትድስ ስቴትስ ጋር በመሆን በቻይና መንግሥት ይደገፋሉ ያሉትን “በበይነ መረብ ወይም ሳይበር ላይ የሚፈጸመውን የጥፋት ድርጊት” አውግዘዋል፡፡

“ማይክሮሶፍት ኤክስቼንጅ” በተባለው የኤሜል ልውውጥ መገልገልያ መረብ እና ቋት ላይ፣ የተፈጸመው ጥቃት የታወቀው፣ ባላፈው ጥር ወር ነበር፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን አካውንት መበከል የጀመረው ደግሞ፣ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ ፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር እየተካሄደ ላለው ለዚህ የሳይበር ጥቃት ቻይናን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ቤጂንግ ግን ክሱን የፈጠራ ወሬ ነው ብላዋለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጃን እንዲህ ብለዋል፡፡

“ቻይና አንድ ጊዜ እንደገና አበክራ መናገር ትፈልጋለች፡፡ ዩናይትድ ስቴትስና ሸሪኮችዋ የሳይበር ስርቆትና የሳይበር ጥቃትን አስመልክቶ ቻይናን ኢላማ ማድረጋቸውን እንዲያቆሙ ትጠይቃለች፡፡ ሳይበር ደህንነትን በሚመለከት ቻይና ላይ የምትረጩትን ጥቀርሻ ውሃችሁን አቁሙ፡፡”

ባለፈው ሰኞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የቻያን መንግሥት፣ የበይነ መረቡን ወይም ሳይበር ጠላፊዎችን ትከላከ ልላቸዋለች በማለት እንደሚከተለው ወቅሰዋታል፡፡

“የቻይና መንግሥት እንደሩሲያ መንግሥት ራሳቸው አያደርጉትም፣ ድርጊቱን የሚፈጸሙትን ግን ይከላከሉላቸዋል፡፡ ምናልባትም ድርጊቱን እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸዋል፡፡”

የኔቶ አባል አገራት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ጃፓን ፣ እና ኒው ዘላንድ፣ የሳይበር ጥቃትን ትደግፋለች በሚል ቻይናን በመክሰስ ረገድ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ተባባሪ ሆነዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስም አሜሪካንና ሌሎች አገሮችን ኢላማ በማድረግ፣ በመንግሥት ከተደገፈው የሳይበር ጥቃት ጋር፣ ግንኙነት አላቸው በሚል፣ አራት የቻይና ዜጎች ላይ ክስ መስርታለች፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ፣ የካሊፎኒያ ደቡባዊ ግዛት አቃቤ ህግ፣ ራንዲ ግሮስማን፣ ስለ ተከሳሾቹ እንዲህ ይላሉ

“ከተከሱስት አራቱ ሰዎች ውስጥ፣ ሶሶቱ በቻይና መንግሥት ደህንነት ሚኒስቴር ወይም MSS ተብሎ በሚጠራው ተቋም ውስጥ የሚሰሩ መኮንኖች ናቸው፡፡ መንግሥትን ስራ ለመደበቅ ፣ ለሽፋን በተቋቋሙ ኩባንያዎች አማካይነት የተባለውን የሳይበር ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ናቸው፡፡”

ይሁን እንጂ ግን የባይደን አስተዳደር ባለፈው ወር በተፈጸመው የሳይበር ጥቃት፣ በሩሲያ መንግሥት ላይ እንደወሰደው የአጸፋ እርምጃ፣ ቻይናን፣ እንደ ሩሲያ በማዕቀብ ወይም ዲፕሎማቶችን በማባረር አልቀጣም፡፡

በውጭ ግንኙነት ማዕክል የዲጂታል እና ሳይበር ስፔስ ፖሊሲ ፕሮግራም ዳይሬክተር አዳም ሴገል፣ የዚህ ምክንያት ነው፣ ያሉትን እንደሚከተለው ይገልጹታል

ቻይና የማይክሮሶፍት ኢሜል መገልገልያን አልጠለፍኩም አለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

“ቻይና ምናልባትም ቻይና ውስጥ የሚሰሩ የዩናትድ ስቴትስ ቢዝነስ ድርጅቶችን ልትበቀል ትችላለች ብለው ሰግተዋል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ምናልባትም ከአጋር አገሮች ውስጥ በቂ ተባባሪ ማግኘት ሊያስቸግር ይችላል፡፡ ከቻያና ጋር የኢኮኖሚ ትስስር ካላቸው የአውሮፓ አገሮች ውስጥ በቻይና ላይ እንዲጣል ለሚፈለገው ማዕቀብ ተባባሪ የሚሆኑ ቁጥራቸው አነስተኛ ሊሆን ይችላል፡፡”

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄኒ ሳኪ በውጭ ኃይሎች የሚደረገው የሳይበር ጥቃት ላይ የሚደረገው ምርመራ በመካሄድ ላይ ያለ መሆኑን ገልጸው ወደፊት የሚወሰደውን እርምጃ በሚመለከት የተቋጨ ነገር አለመኖሩን ይናገራሉ

“ይህ ከቻይና ወይም ከሩሲያ ጋር የሳይበር ደህንነትን አስመልከቶ የምናደርገው የመጨረሻ ጥረት አይደለም፡፡”

ቻይና የትኛውንም የሳይበር ጥቃቶች የምታቀውም መሆኑን ገልጻ፣ ብዙዎቹ የሳይበር ጥቃቶች የሚመነጩት ከዩናይትድ ስቴትስ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

ተንታኞች እንደሚሉት ደግሞ፣ የሳይበር ጥቃት ዩናይትድ ስቴትን ጨምሮ፣ በቻይና እና ሩሲያ፣ ተዘውትሮ የሚፈጸም ሲሆን፣ ድርጊቱም የሚቆም አይመስልም ፡፡

አሁንም በውጭ ግንኙነት ማዕክል፣ የዲጂታል እና ሳይበር ስፔስ ፖሊሲ ፕሮግራም ዳይሬክተር፣ አዳም ሴገል እንዲህ ይላሉ

“የመረጃ ቋቶችንም ይሁን ሥርዐቶችን ጨርሶ በማጥፋት የሚደረገውን ጥቃትም ሆነ ማስተጓጎልን በሚመለከት ከአንድ ስምምነት ላይ እንደምንደርስ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ኮሎኒያል በተባለው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተካሄደው ጥቃት ድርጅቱ ለበርካታ ቀናት የማስተላለፊያ መስመሩን ከአገልግሎት ውጭ እንዲያደርግ አድርጎታል፡፡ ከቻይናም ሆነ ከሩሲያ ጋር ካንድ ስምምነትም ሆነ የጋስራ አሰራር እንድርስ የሚያስደርገን ይህ ዓይነቱ ጥቃት ነው፡፡”

እኤአ በ2015 የቀድሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና የቻይናው መሪ ዢ ጄፒንግ ሁለቱ አገሮች የሳይበር ጥቃትን በጋራ ለመመከት እና በግዛቶቻቸው ውስጥ የሚፈጠሩትን ጥቃቶች ለመመርመር ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ግን አሁን በቅርቡ የተካሄደው የሳይበር ጥቃት በሁለቱ አገሮች፣ በቻይናና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው እንደሚችል ተገምቷል ፡፡

የቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG