በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በኩባ የስለላ ጦር ሰፈር አቋቁማለች መባሏን ውድቅ አደረገች


ፎቶ ፋይል፦ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ፣ የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ
ፎቶ ፋይል፦ የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ፣ የኩባ ፕሬዚዳንት ሚጉዌል ዲያዝ-ካኔል ቤርሙዴዝ

ቻይና፣ በኩባ፥ የስለላ የጦር ሰፈር አቋቁማለች፤ የሚለውን የዩናይትድ ስቴትስ ክሥ፣ ዛሬ ሰኞ ውድቅ አድርጋለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ወንቢን፣ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ክሥ፥ ወጥነት የጎደለው እና እርስ በርሱ የሚቃረን ሐሳዊ መረጃ ነው፤ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

የዋንግ አስተያየት የተሰማው፣ የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣን፣ ቻይና ከኩባ ውጭ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ከኾነችው ፍሎሪዳ፣ 200 ኪ.ሜ. ያህል ርቆ በሚገኝ ሥፍራ፣ ለተወሰነ ጊዜ የስለላ ሥራዎችን ስታካሒድ ቆይታለች፤ በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው፡፡

ባለፈው ቅዳሜ፣ የኩባ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካርሎስ ፈርናንዴስ ደ ካሲዮ፣ ክሡን፥ “ስም የሚያጎድፍ መላምት ነው፤” ሲሉ፣ በትዊተር ገጻቸው ነቅፈውታል ፡፡

የሁለቱ ሀገራት መካሠሥ የተደመጠው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በቅርቡ ወደ ቤጂንግ ለመጓዝ እየተዘጋጁ ባሉበት ጊዜ ነው፡፡

ብሊንከን፣ ባለፈው የካቲት ወር፣ ወደ ቻይና ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰርዘዋል፡፡

ጉብኝቱ የተሰረዘው፥ አንድ ትልቅ የቻይና የስለላ ፊኛ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ሰማይ ላይ ከመብረሩ ጋራ በተያያዘ፣ በሁለቱ አገሮች መካከል የነበረው ውጥረት በመካረሩ እንደኾነ ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG