በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ለመዋጋት ዕቅድ ይፋ አደረጉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን

የዓለም ባለግዙፍ ኢኮኖሚዎች እና ትልቁን የአየር በካይ ካርቦን ልቀት የሚያደርሱት ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የየበኩላቸውን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል

ትናንት የቻይና ፕሬዚዚንት ሲ ዢንፒንግ ሃገራቸው በውጭ ሃገሮች በከሰል ሃይል የሚንቀሳቀሱ የኃይል ማመንጫ ተቋማትን በገንዘብ እንደማትደግፍ አስታውቀዋል። ባለፈው ዓመትም በጠቅላላው ጉባኤ ላይ አየር ንብረት ለውጥን አስመልክተው ጉባኤውን ያስገረመ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ቀደም ብለው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ደሆች ሃገሮች ንጹህ የሃይል ምንጭ እንዲጠቀሙ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከተሉ ችግሮችን እንድቁዋቁዋሙ ለመርዳት ሃገራቸው የምትሰጠውን የገንዘብ ርዳታ እስከ 2024 ዐመተ ምህረት በሚኖረው ጊዘ በዕጥፍ በማሳደግ አስራ አንድ ነጥብ አራት ብሊዮን ዶላር እንደምትመድብ ይፋ አድርገዋል

XS
SM
MD
LG