በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ቆጠራና ኢትዮጵያውያን


በዩናትድ ስቴትስ በየአስር ዓመቱ አንዴ የሚደረገው የህዝብ ቆጠራ ዘንድሮም ይካሄዳል፡፡ የቆጠራው መጠናቀቂያ ጊዜ ከህዳር ወደ መስከረም እንዲያጥር በመደረጉ ሊጠናቀቅ የቀሩት ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ምን ይመስላል?

ወ/ሮ ሀመራዊት ተስፋ የሚሰሩት ሜሪላንድ በሚገኘው የሞንት ጎመሪ ኮሌጅ ሲሆን አቶ አቶ ኤልያስ ደግሞ ከሜሪላንድ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማዕከል ናቸው፡፡ ሁለቱም ትውልደ ኢትዮጵያውን በህዝብ ቆጠራው ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚሰራው ግብረ ኃይል ውስጥ በመሆን ማህበረሰቡን በማስተባበር ላይ ይገኛሉ፡፡ የቆጠራው ጊዜ መጠናቀቂያ የቀረው ጥቂት ስለሆነ ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ እስካሁን ራሳቸውን ያላስቆጠሩና በቆጠራው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የሚታሰቡ ወገኖች በቀሪው የሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ተሳታፊ ካልሆኑ እድሉ ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት እንዳመለጣቸው ይቆጠራል፡፡ ባይ ናቸው የዛሪዎቹ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ እንግዶቻችን አቶ ኤልያስ ወልዱና ወ/ሮ ሀምራዊት ተስፋ፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ

የዩናትድ ስቴትስ ቆጠራና ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:04 0:00


XS
SM
MD
LG