በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዳዕሽ መሪዎች


ሶርያ ያሉት ከፍተኛ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን በአረብኛ አጠራሩ ዳዕሽ መሪዎች ላይ ወረራ እየተካሄድ መሆኑ ታውቋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች የአሸባሪው ቡድን ቁልፍ ሰዎችን ለማጥፋት ተከታታይ ወረራዎች እያካሄደ መሆኑን ትናንት ገልጿል። የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች የዳዕሽ መሪ የነበረውን አቡ ባካር ዐልባግዳዲንና ቃል አቀባዩ አቡ ሐሰን አል-ሙሐጂርን በመግደል ተግባር የረዳ መሆኑ ተገልጿል።

የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ቃል አቀባይ ሙስታፋ ባሊ “ከግድያ የተረፉት የዳዕሽ አማጽያን ከእሥር አያምልጡም” ሲል በትዊተር ዝቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ባሽራ ሶርያ የነበረውን ግቢ ወራ ወደ ዋናው የዳዕሽ መሪ ሞት ያደረሰውን እርምጃ ለመውሰድ የቻለችው የሶርያ ዲሞክራስይዊ ሃይሎች በተጫወተው አብይ ሚና ምክንያት ነው በማለት አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ካሞገሱ በኋላ ነው በዳዕስ ላይ ወረራ እያካሄደ መሆኑን የሶርያው ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ያስታወቀው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG