በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ትረምፕ በምርጫው መሸነፋቸው ግልጽ ሲሆን ንዴታቸው እየተባባሰ ሄደ" የቀድሞ የኋይት ሀውስ ረዳት የምስክርነት ቃል


የቀድሞዋ የኋይት ሀውስ ጽ/ቤት ሹም ረዳት ካሲዲ ሀቺንሰን
የቀድሞዋ የኋይት ሀውስ ጽ/ቤት ሹም ረዳት ካሲዲ ሀቺንሰን

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እኤአ በ2020 በድጋሚ በተወዳደሩበት ምርጫ ሽንፈት ከገጠማቸው ወዲህ ብስጭታቸው እየጨመረና በአደገኛ ሁኔታ ተቆጭና በጸባያቸውም ተለዋዋጭ እየሆኑ መጥተው ነበር ሲሉ የቀድሞዋ የኋይት ሀውስ ጽ/ቤት ሹም ረዳት ካሲዲ ሀቺንሰን ለጥር ስድስት አመጽ መርማሪ ምክር ቤታዊ ኮሚቴ በሰጡት ቃል ተናገሩ፡፡

ኻቺንሰን ትራምፕ የምርጫውን ውጤት ለማገድ ያልፈለጉትን ም/ፕሬዚዳንቱን ማይክ ፔንስ "ስቀለው" ሲሉ ከነበሩትና በምክር ቤቱ ህንጻ ላይ ጥቃት ካደረሱት አመጸኞቹ ደጋፊዎቻቸው ጋር ተስማምተው ነበር ብለዋል፡፡

በምክር ቤቱ ፊት ለፊት ከተሰለፉት በሺዎቹ ከሚቆጠሩ የትራምፕ ደጋፊዎች አንዳንዶቹ “ማይክ ፔንስ ይሰቀሉ” የሚሉ መፈክሮችን ባሰሙበት ወቅት ትራምፕ “ማይክ ይገባዋል” ብለው “ለአለቃዬ ለኋይት ሀውስ ጽ/ቤት ሹም ለማርክ ሜዶውስ ሲናገሩ ሰምቻለሁ” ብለዋል ሀቺንሰን በሰጡት የምስክርነት ቃል፡፡

“የጸረ ፔንስ ተቃዋሚዎች ያን መፈክር ሲያሰሙ ምንም ጥፋት መስሎ አልተሰማቸውም” ብለው አለቃቸው ሜዶውስ በወቅቱ ነግረዋቸው እንደነበር ካንቺንሰን አስታውሰዋል፡፡

ማይክ ፔንስ በወቅቱ በተቃዋሚዎቹ ቁጥጥር ስር ውሎ በነበረው የምክር ቤቱ ህንጻ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም ጠባቂዎቻቸው ደህንነታቸው ወደሚጠበቅበት ሥፍራ አስቀድመው ወስደዋቸው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG