በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በነገው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ላይ የታለሙ የሀሰት መረጃ ሊባባሱ እንደሚችሉ ተገለጠ


በዩናይትድ ስቴትስ ነገ ማክሰኞ በሚካሄደው የአጋማሽ ፕሬዚዳንታዊ ዘመን ምርጫ ድምጽ መስጫ
በዩናይትድ ስቴትስ ነገ ማክሰኞ በሚካሄደው የአጋማሽ ፕሬዚዳንታዊ ዘመን ምርጫ ድምጽ መስጫ

በዩናይትድ ስቴትስ ነገ ማክሰኞ በሚካሄደው የአጋማሽ ፕሬዚዳንታዊ ዘመን ምርጫ በድምጽ መስጫ ማሺኖች እና ስለድምጽ አሰጣጥ ሥርዓቱ ላይ ጥርጣሬ ለማሳደር የታለመ አዲስ ዘመቻ ሊከፈት እንደሚችል ተገለጸ።

የምርጫ ደህንነት፥ የሳይበር ሴኩሪቲ እና የመሰረተ ልማት ደህንነት መስሪያ ቤት (ሲአይኤስኤ) ኃላፊዎችን ጨምሮ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ወቅት የሚሰሙት የተዛቡ መረጃዎች እአአ በ2020 የነበሩትን እና ፉርሽ የተደረጉትን አሳሳች መረጃዎች የሚያስተጋቡ ናቸው በማለት ሲያጣጥሉ ቆይተዋል። ዋይት ሀውስም ይህንኑ መልዕክት አስተጋብቷል።

የብሔራዊ ጸጥታ ምክር ቤት የስትራተጂያዊ ግንኙነቶች አስተባባሪው ጃን ከርቢ ባለፈው ዐርብ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "አሜሪካውያን ይህ ምርጫ ነጻ ፍትሃዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አስፈላጊው ሁሉ መከናወኑን በመተማመን ወደምርጫ ጣቢያ መሄድ ይችላሉ መሄድም አለባቸው ብለን እናምናለን" ብለዋል።

ይሁን እንጂ ሬከርድድ ፊውቸር የተባለ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ኩባኒያ ባወጣው አዲስ ጥናት በምርጫው ዕለት እና ከዚያም በሚቀጥሉት ቀናት ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው ደረጃም ባይሆን ድምጽ መስጫ ማሽኖች እና የድምጽ አሰጣጥ ስርዓቱ ላይ ያነጣጠረ የሀሰት መረጃ መባባሱ እንደማይቀር ምልክቶች እንዳሉ ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG