በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ እና ካናዳ ድንበር ላይ የፈነዳው መኪና ከሽብር ጥቃት ጋር እንደማይየያዝ ተገለጸ


ሬይንቦው ድልድይ የፍተሻ ጣቢያ ጭስ ይታያል፣ እአአ ኅዳር 22/2023
ሬይንቦው ድልድይ የፍተሻ ጣቢያ ጭስ ይታያል፣ እአአ ኅዳር 22/2023

በትናንትናው ዕለት በአሜሪካ እና በካናዳ ድንበር መሃል የፈንዳው መኪና ከሽብርተኞች ጥቃት ጋር እንደማይየያዝ የበፈሎ፣ ኒው ዮርክ አቃቤ ሕግ ዛሬ አስታውቋል።

መኪናው ከፍጥነት በላይ ከበረረ በኋ፣ በአየር ላይ ተንሳፎ ሁለቱ አገራት ከሚያገኛነው ሬይንቦው ድልድይ አቅራቢያ ተከስክሶ ሲፈነዳ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።

ባለሥልጣናት ጉዳዩ እስከሚጣራ በአካባቢው ያሉትን ኬላዎች በሙሉ ዘግተዋል። የፍንዳታው ምክንያት እስካሁን ባይታወቅም፣ ከሽብር ጋር እንደማይየያዝ ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው።

የአሜሪካው የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በአሜሪካ ድንበር በኩል በፈነዳው መኪና ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG