በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

36.5 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምፅ ሰጥተዋል


ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፊታችን ማክሰኞ ይካሄዳል።

የዕጩ ተፎካካሪዎቹ ዲሞክራትዋ ሂላሪ ክሊንተንና ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ዘመቻዎች በዚህ የመጨረሻው የተጧጧፈ ዘመቻ ሳምንት መጨረሻ መራጮችን ለመቀስቀስ በዋና ዋናዎቹ የብርቱ ፍልሚያ ወረዳ ክፍለ ግዛቶች እየተዘዋወሩ ናቸው።

በአንድ አዲስ የመራጭ አስተያየት ግምገማ መሠረት እጅግ ብዝሃኑ መራጭ በሁለቱም ተፎካካሪዎች ተንገፍግፉዋል። ያም ቢሆን ሚሊዮኖችን ገፍቶ

"ድምፅ ባልሰጥስ፣ ቢቀርብኝ" የሚያሰኝ ደረጃ አላደረሳቸውም ።

ሂላሪ ክሊንተን
ሂላሪ ክሊንተን

ኒውዮርክ ታይምስ እና ሲቢኤስ ኒውስ ባካሄዱት ግምገማ ሠማኒያ ከመቶው መራጭ

"እነዚህ ሁለቱ ዕጩዎች አንገሸገሹኝ" ብሉዋል፡፡

ያም ሆኖ የዩናይትድ ስቴትስ የምርጫዎች ፕሮጀክት የተባለ አካል ባወጣው መረጃ መሰረት እስካሁን ከሠላሳ ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ከወዲሁ ድምፅ ሰጥተዋል።

ሁለቱ ዕጩዎች እጅግ በተቀራረበ የመራጭ ድጋፍ እየተፎካካሩ ባሉበት በነዚህ የምርጫው ዋዜማ ጥቂት ቀናት፣ የሚወራወሩት እሰጥ እገባ ይበልጡን እየሰላ መጥቱዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

36.5 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን ድምፅ ሰጥተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

XS
SM
MD
LG