በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሊፎርኒያ ከባድ ዝናብ ጉዳት ማድረሱን እንደቀጠለ ነው


በጭቃ ጎርፍ የተያዘ ተሽከርካሪ በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ፣ እአአ የካቲት 5/2024
በጭቃ ጎርፍ የተያዘ ተሽከርካሪ በሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ፣ እአአ የካቲት 5/2024

በካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ አካባቢ ለሁለት ቀናት ከባድ አውሎ ነፋስን ቀላቅሎ በወረደው ከባድ ዝናብ ወደ 400 በሚጠጉ ቦታዎች ላይ ከጭቃ ጎርፍ ጋር የተያየዘ የመሬት መንሸራተት መድረሱ ተነገረ፡፡

በሁለት ቀናት ውስጥ ጥሏል የተባለው ዝናብ በአንድ የዝናብ ወቅት ሊገኝ ከሚችለው ከፊሉ ያህል እንደሆነ ተገልጧል፡

ከባዱ አውሎ ነፋስና ዝናብ አዳዲስ አደጋዎችን ሊያስከትል እንደሚችል ማስጠንቀቂያዎች እየደረሱ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ትንበያ አገልግሎት ትንሽ ቆየት ብሎ ይሰርዘው እንጂ ሳንዲያጎ አውራጃ አይታው የማታውቀውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ምንም እንኳ ኣውሎ ነፋስ እጅግ የከበደ ቢሆንም በሎስ አንጀለስ ከባድ አደጋዎች እና ሞት አለመድረሱ ተዘግቧል፡፡

የሎስ አንጀለስ ከንቲባ ካረን ባስ ነዋሪዎቹ ማስጠንቀቂያዎቹን ሰምተው ከጎዳና ውጭ በመቆየታቸው አመስግነው ዝናቡ ይቆምበታል እስከተባለበት ጊዜ ድረስ ይህንኑ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የጭቃ ናዳዎች በደረሱባቸው 383 ቦታዎች እንዲሁም ከነዋሪዎች ውጭ እንዲሆኑ በተደረጉ ሰባት ህንጻዎች ላይ የነፍስ አድን ምላሽ መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG