በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካን የብድር ጣሪያ የሚያነሳውና መንግስት ወጪወችን እንዲቀንስ የሚደነግግ ህግ ጸደቀ


የህግ መወሰኛው ምክር ቤት
የህግ መወሰኛው ምክር ቤት

የዩናይትድ ስቴይትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱን የብድር ጣሪያ ከፍ የሚያደርገውንና በምትኩ ደግሞ መንግስት ወጪ እንዲቀንስ የሚደነግግ ህግ ሰኞ አመሻሹ ላይ አጸደቀ። ህጉ የጸደቀው አገሪቱ የተቆለለባትን 14.3 ትሪሊዮን ብድር መክፈል ከማያስችላት ቀውስ ከመግባቷ አንድ ቀን ቀድማ ነው።

ኦባማ የአገሪቱን የብድር ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፤ በዚህም አገሪቱ ልትገባበት የነበረውን ዕዳን ያለ መክፈል ቀውስ አስወግዳለች።

የተፈረመው ህግ የአገሪቱን የመበደር ገደብ ከ14.3 ትሪሊዮን በላይ ሲያደርግ የመንግስት ወጪ ደግሞ እንዲቀንስ ይደነግጋል። የሁለቱም ፓርቲወች በሚያስማማ ሰጥቶ መቀበል መርህ የተረቀቀውና በፕሬዚዳንት ኦባማ የጸደቀው ይህ ህግ ወደ አልተጠበቀ ቀውስ አገሪቱ እንዳትገባ ያደርጋል ተበሎ ይታመናል።

የዩናይትድ ስቴይትስ ሴኔት በዛሬውለት የአገሪቱን የበጀት መጓደል ለማስተካከል መንግስት ወጭውን እንዲቀንስና ተጨማሪ ብድር እንዲያገኝ የሚያስችል ህግ አጸደቀ።

ሃምሌ 26 2003ዓም የዩናይትድ ስቴይትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት ተጨማሪ ብድር ካላገኘ፤ አገሪቱን የሚያንቀሳቅስበትና ብድሩን የሚከፍልበት የገንዘብ አቅሙ እንደሚሟጠጥ ካስታወቀ ቆይቷል።

ዩናይትድ ስቴይትስ ልትበደር የምትችለው የ14.3 ትሪሊዮን ዶላር ጣራ ላይ በመድረሷ፤ ተጨማሪ ብድር ለማግኘትና የቆዩ ብድሮችን ለመክፈል የባራክ ኦባማ አስተዳድር በኮንግረስ የብድር ጣራው እንዲነሳለት ጠይቋል።

አሜሪካ ይሄን ማድርግ ካልቻለች ተበድራ በዚህ ቀን እከፍለዋለሁ ያለችውን ገንዘብ፤ ቃሏን ጠብቃ በቀኑ መክፈል ይሳናታል። የኦባማ አስተዳድር፤ የሄ ከሆነ የዩናይትድ ስቴይትስ ብቻ ሳይሆን የአለም ኢኮኖሚ ይናጋል እያለ ሲከራከር ቆይቷል።

ሪፐብሊካኖች በበኩላቸው፤ መንግስቱ በዜጎች ላይ ቀረጥ እንዳይጭንና የበጀት መጓደሉን፤ ተጨማሪ የበጀት ቅነሳ በማድረግ ሊያስተካክል ይገባዋል ሲሉ ሲከራከሩ ሰንብተዋል።

በትናንትናውለት በህግ መምሪያው የህዝብ ተወካዮች የብድር ጣራውን የሚያነሳና፤ የመንግስቱን በጀት የሚቀንስ ህግ አሳልፏል። ዛሬ የህግ መወሰኛው ሴኔት ውሳኔውን አጽድቋል፤ ፕሬዝደንት ኦባማ እንዲፈርሙት ባስተላለፈው መሰረት በፊርማቸው ዛሬ አጽድቀዋል።

በዚህ አወዛጋቢ የበጀት ጉዳይ የባለሙያ አስተያየት ይዘናል። በሃርፐር ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑ ጌታቸው በጋሻው ማብራሪያ ይሰጡናል።

XS
SM
MD
LG