በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፈ-ጉባዔ ጆንሰን የዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮን ድንበር ጎበኙ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ኢግል ፓስ እአአ ጥር 3/2024
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን፣ የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ኢግል ፓስ እአአ ጥር 3/2024

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን ወደ 60 የሚጠጉ የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር ቤት አባላትን በመምራት ትናንት ረቡዕ የዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮን ድንበር ጎብኝተዋል፡፡

ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ወደሚገኘው ኢግል ፓስ የተደረገው ጉዞ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን እና እስራኤልን ጨምሮ ለአደጋ ጊዜ ካቀረቡት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎች ጋር ጠንካራ የፍልሰተኞች ጉዳይ ፖሊሲዎች እንዲወጡ ጫና ለማሳደር መሆኑ ተነግሯል፡፡ አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን "ፕሬዚዳንት ባይደን በብሄራዊ ደህንነት ላይ ላተኮረው ወጪ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ከፈለጉ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት በመጠበቅ ቢጀምሩ ይሻላል። ያ የሚጀምረው ልክ እዚህ ደቡብ ድንበራችን ላይ ነው።" ብለዋል፡፡

ጆንሰን ሁለቱም ፓርቲዎች የምክር ቤት አባላት የተስማሙበትን በጀት ስለመደገፋቸው ያላቸውን የጠነከረ ጥርጣሬ እየገለጹ ነው፡፡

እየቀረበ ያለውን ለመንግስት በጀት ውሳኔ የሚሰጥበት ቀነ-ገደብ እንደ ተጨማሪ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉም እያመላከቱ ነው።

በዋሽንግተን የሚገኙ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ተደራዳሪዎች ግን የሁለትዮሽ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስፋ አድርገዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ እና የሜክስኮ ባለሥልጣናት እየሻቀበ የመጣውን የፍልስተኞች ቁጥር ለመቀነስ እኤአ ታህሳስ 28 ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ሁለቱን አገሮች በሚያዋስነው የጋራ ድንበር በኩል በዚህ የታህሳስ ወር ውስጥ በየቀኑ 10ሺ የሚደርሱ ህገወጥ ፍልስተኞች ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡

ህግ አውጭዎቹ ሪፐብሊካኑ የምክር ቤት አባላት ለዩክሬን፣ እስራኤል እና ታይዋን የሚሰጡትን ወታደራዊ ድጋፎች በሚያካትተው የስደተኞቹ ህግ ላይ ለውጦች እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG