በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሥራ አንደኛ ቦምብ የያዘ እንደሆን የሚጠረጠር የፖስታ ጥቅል መገኘቱ ተገለፀ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አሥራ አንደኛ ቦምብ የያዘ እንደሆን የሚጠረጠር የፖስታ ጥቅል መገኘቱን የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ አስታወቀ። ይሄኛው በዲሞክራቱ ሴኔተር ኮሪ ቡከር አድራሻ የተላከ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ አሥራ አንደኛ ቦምብ የያዘ እንደሆን የሚጠረጠር የፖስታ ጥቅል መገኘቱን የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ አስታወቀ። ይሄኛው በዲሞክራቱ ሴኔተር ኮሪ ቡከር አድራሻ የተላከ ነው።

ኤፍቢአይ እንዳለው ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ለሌሎችም ታዋቂ ዲሞክራቶች እና የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ነቃፊዎች የተላኩትን ቦምቦች የያዙትን ጥቅሎች ጋር ተመሳሳይ ነው። ይሄኛው የተገኘው ፍሎሪዳ ውስጥ መሆኑን ህግ አስከባሪዎች ገልጸዋል።

ሲኤንኤን እና ሌሎችም የብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት ለቀድሞ የብሄራዊ ፀጥታ ዳይሬክተር ጄምስ ክላፐር የተላከ አሥራ ሁለተኛ ተጠርጣሪ ጥቅል ዛሬ ተገኝቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG