በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ሜክሲኮን ጎበኙ


የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሴሎ ኢብራርድ፣ ለየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቤኒቶ ጁዋሬዝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ሲደርጉላቸው።
የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሴሎ ኢብራርድ፣ ለየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቤኒቶ ጁዋሬዝ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ሲደርጉላቸው።

በስደተኞችና አሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ሻክሮ የነበረውን ግንኙነታቸውን ለማደስ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሜክሲኮን በመጎብኘት ላይ ናቸው።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሜክሲኮው ፕሬዚዳንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ጋር ተገናኝተው ሲነጋገሩ ዋና አጀንዳቸው ስደተኞችን የተመለከተ እንደነበር የቪኦኤው ናይክ ቺንግ ከሜክሲኮ ከላከው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

“ኢ-መደበኛ የሆነ ስደትን በተመለከተ ህጋዊ የሚሆንበትንና ሰብዓዊ የሆነ የድንበር አስተድደርን በተመለከተ ባሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ስለምናደርገው ጥረት ተነጋግረናል” ብለዋል ብሊንከን በጋዜጣዊ መግለጫቸው።

“ስደትን በተመለከተ የችግሩን ምንጭ ከዚህ በፊት ሜክሲኮና ዩናይትድ ስቴትስ ተባብረው በማያውቁበት ደረጃ ተንጋግረናል” ሲሉ አክለዋል ብሊንከን።

ሜክሲኮ ለአሜሪካ ከሶስት ዋና የንግድ ሸሪክ ሃገሮች አንዷ ስትሆን፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት አሜሪካ ምርቷን ከምትልክባቸው ሃገሮች ሜክሲኮ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበረች።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚሉት፣ ህገ ወጥ ስደተኞች ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ድንበር መሻገራቸው በተቀባይ ሃገሯ ላይ ጫና ፈጥሯል።

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የቴክሳስ ግዛት ያለበትን ሸክም ለማቃለል በሚል ስደተኞችን በአውቶብስ እየጫነ ወደ ኒው ዮርክና ዋሽንግተን ልኳል።

የብሊንከን የሜክሲኮ ጉብኝት የመጣው ፕሬዚዳንት ባይደን የሜክሲኮ አቻቸውን በነጩ ቤተ መንግሥት ተቀብለው ባነጋገሩ በሁለተኛው ወር መሆኑ ነው።

የሜክሲኮ የኃይል ኩባንያዎች በመንግሥት ሥር ያሉና በመንግሥት ድጋፍ ስለሚደረግላቸው የአሜሪካ የግል ኩባንያዎችን ተወዳዳሪነት የሚጎዳና፣ ከንግድ ሥምምነት ያፈነገጠ ነው በሚል አሜሪካ ቅሬታዋን በሜክሲኮ ላይ ስታሰማ ቆይታለች።

ባለፈው ሰኔ በዩናይትድ ስቴትስ የተዘጋጀውን “ዘ አሜሪካስ ጉባኤ” ኩባን፣ ኒካራጐጓን እና ቬኔዝዌላን ያገለለ ነው በሚል የሜክሲኮው ፕሬዚዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር ሳይገኙ ቀርተዋል።

XS
SM
MD
LG