በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ትንኮሳዋን እንድታቆም ብሊንከን አሳሰቡ


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን

“ቻይና በታይዋን ላይ ከምትፈጽመው ወታደራዊ ትንኮሳ ትታቀብ ሲሉ” የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ዓርብ አስጠንቅቀዋል።

የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማስጠንቀቂያ የመጣው የራስ ገዟ ታይዋን መሪ ከቻይና በተለየ ቀን የሚከበረውን ብሔራዊ የነፃነት በዓል አስመልክቶ ላደረጉት ንግግር ቤጂንግ ከረር ያለ ምላሽ መስጠቷን ተከትሎ ነው።

ቪየንቲያን በተሰኘችው የላኦስ ከተማ በተደረገው የምሥራቅ እስያ ጉባኤ ላይ የተገኙት ብሊንከን፣ በታይዋን የባሕር ወሽመጥ አካባቢ መረጋጋት እንዲኖርና ያሉትን ሁኔታዎች የሚቀይር እርምጃ በሁለቱም ወገን እንዳይወሰድ የደቡብ ምሥራቅ እስያ ሃገራት ማኅበር አባላትና የሌሎችም አጋራት ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል።

ታይዋን የቻይና ሪፐብሊክ ምሥረታ በእ.አ.አ 1912 ነው በሚል፣ በኦክቶበር (ጥቅምት) 10፣ የምታከብር ሲሆን፤ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ደግሞ የሃገሪቱ ምሥረታ 1949 ነው በሚል ኦክቶበር 1 ቀን ታከብራለች፡፡

ትላንት ኦክቶበር 10 ታይዋን በዓሉን በምታከብርበት ወቅት የታይዋኑ ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ ተ ያደረጉት ዓመታዊ ንግግር ቻይናን አስቆጥቶ፣ ዛሬ ዓርብ 20 የሚሆኑ የቻይና ወታደራዊ አውሮፕላኖችና 10 መርከቦች በአካባቢዋ ማንዣበባቸውን ታይዋን አስታውቃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG