በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ለእስራኤል ድጋፋቸውን ገለጹ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በጃፓን-ቶኪዮ እአአ ኅዳር 8/2023
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በጃፓን-ቶኪዮ እአአ ኅዳር 8/2023

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በጃፓን-ቶኪዮ ባደረጉት ጉባኤ፣ ሐማስን በማውገዝ እና እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት አጽንዖት በመስጠት፣ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በተጨማሪም፣ በጋዛ ሰርጥ ችግር ላይ ለወደቁ ሰላማውያን ሰዎች ርዳታ ማድረስ ይቻል ዘንድ፣ ከውጊያው “የሰብአዊ እፎይታ” እንዲወሰድ ጠይቀዋል።

የጋራ አቋማቸውን ያስታወቁት፥ የእንግሊዝ፣ የካናዳ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የጃፓንና የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደኾኑ ታውቋል።

“በጋዛ ያለውን አስቸኳይ የሰብአዊ ኹኔታ አስመልክቶ በጥልቅ ተወያይተናል። በጋዛ ሲቪሎችን መርዳት ይቻል ዘንድ፣ ዜጎቻችንና ሌሎችም የውጪ ዜጎች እንዲወጡ ለማስቻል፣ እንዲሁም ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማመቻቸት፣ ከውጊያው ‘የሰብአዊ እፎይታ’ እንዲወሰድ ኹላችንም ተስማምተናል፤” ብለዋል ብሊንከን።

ከውጊያው እፎይታ እንዲወሰድና በፍልስጥኤማውያን ሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እንዲቀንስ፣ ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋራ ስላደረጉት ንግግር፣ ብሊንከን ለአቻዎቻቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል። እስራኤል ከሐማስ ጥቃት በፊት ወደነበረው ኹኔታ መመለስ እንደማትሻ እንደተገለጸላቸውም ብሊንከን አልሸሸጉም።

ብሊንከን፣ በእስያ የሚያደርጉትን ጉብኝት በመቀጠል፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሶል-ደቡብ ኮሪያ እንደሚገቡና በመጪው ቀናትም ወደ ሕንድ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG