በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ከሰሜን ኢትዮጵያው በተጨማሪ የኦሮሚያው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ተናገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋራ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋራ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋራ ዛሬ ተገናኝተው በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ላይ በተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ለተፈፀሙ አሰቃቂ ድርጊቶች ተጠያቂነት እንደሚያስፈልግ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መሪዎቹ አካታችና ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህ ሊኖር እንደሚገባም መወያየታቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዩናይትድ ስቴትስ ያገኝ የነበረው የኢኮኖሚ እና ሌሎች እርዳታዎች እንዲመለሱ ለማድረግ ዝግጁ ቢሆንም መንግሥት በግጭቱ ወቅት በሁሉም ወገኖች የተፈፀሙትን ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዴት ሊፈታው እንደሚችል ሥጋት አለ።

ከሰሜን ኢትዮጵያ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ እያሳሰባቸው መሆኑን የገለፁት ብሊንከን ችግሩን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ አስረግጠው መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በሁለቱ መሪዎች መካከል ዛሬ የተካሄደው ውይይት በዋናነት በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት መቆም ተከትሎ የግጭት ማቆም ሥምምነቱ ተግባራዊነት ዙሪያ ስለታዩ ከፍተኛ መሻሻሎች ማተኮሩን የገለፁት ፕራይስ ይህ መሻሻል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማቋቋምን እንደሚያጠቃልም አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG