በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የዶሮ እንፍሉዌንዛን ለመዋጋት 1 ቢሊዮን ዶላር ተመደበ


ለሽያጭ የቀረበ እንቁላል በግሮሰሪ በሊንድኸርስት፣ ኒው ጀርሲ፣ እአአ የካቲት 4/2025
ለሽያጭ የቀረበ እንቁላል በግሮሰሪ በሊንድኸርስት፣ ኒው ጀርሲ፣ እአአ የካቲት 4/2025

የአእዋፍ እንፍልዌንዛ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአሜሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎችን በመግደሉና ከፍተኛ የእንቁላል እጥረት በመከሰቱ መንግሥት በሽታውን ለመዋጋትና ከውጪ እንቁላል ለማስገባት 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን የሀገሪቱ የግብርና ምኒስትር አስታውቀዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከሰተው የአእዋፍ እንፍሉዌንዛ 166 ሚሊዮን ዶሮዎች መሞታቸውን የአሜሪካው የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሽታው አንድ ሺሕ የሚሆኑ የወተት ላሞችንና 70 የሚሆኑ ሰዎችንም ማጥቃቱ ታውቋል። ባለፈው ዓመት አንድ ሰው በበሽታው ሞቷል።

አምስት ሚሊዮን ዶላር ለአርቢዎች ነፃ የዶሮ ምርመራ ለማድረግ እንዲሁም 400 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በበሽታው የተያዙ ዶሮዎቻቸውን ለመግደል ለሚሹ አርቢዎች እንደተመደበ የግብርና ምኒስትሩ ብሩክ ሮሊንድ አስታውቀዋል።

ገንዘቡ በባለሀብቱ ኢላን መስክ በተመራው ቡድን በቅርቡ ከግብርና ሚኒስቴሩ ላይ ከተቀነስው በጀት ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።

ወደ ውጪ የሚላከውን እንቁላል በመቀነስና ከውጪ የሚገባውን በመጨመር በእንቁላል ገበያ ላይ የሚታየውን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ዋጋ ለመቀነስ አስተዳደሩ ማቀዱም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG