የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዛሬ 81 ዓመታቸውን ሲያከብሩ፣ በመጪው ሐሙስ ከሚታረዱት ተርኪዎች ሁልቱን ምህረት አድርገውላቸዋል።
የምስጋና ቀን በመጪው ሐሙስ በአሜሪካ እና በሌሎች ጥቂት አገራት የሚከበር ሲሆን፣ ለሁለት ተርኪዎች ምህረት ማድረግ ዓመታዊ ፕሬዝደንታዊ ልምድ ነው።
በዋይት ሃውስ የሚካሄደው ዓመታዊ ሥነ ስርዓት፣ በተከታታይ የሚመጡት ገና እና አዲስ ዓመት እንዲሁም ሌሎች በዓላትን ማስጀመሪያ ተደርጎ ይቆጠራል።
በአሜሪካ ታሪክ ባለ ረጅም ዕድሜ ፕሬዝደንት የሆኑት የጆ ባይደን ባለቤት ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን፣ የባለቤታቸውን ልደት ከማክበራቸው በተጨማሪም፣ ለዋይት ሃውስ የተላከውንና 5.6 ሜትር ርዝመት ያለውን የገና ዛፍም ተረክበዋል።
ለተርኪዎቹ ምህረት የማድረግ ልምዱ የጀመረው በእ.አ.አ 1947 ሲሆን፣ የተርኪ ገበሬዎችን የሚወክለው ብሔራዊ የተርኪ ፌዴሬሽን ለወቅቱ ፕሬዝደንት ሃሪ ትሩማን ተርኪዎችን ባቀረበበት ወቅት ነው።
መድረክ / ፎረም