በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የእስራኤል ሐማስ ጦርነት በተመከለተ ከአምስት ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን

በድጋሚ የታደሰ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ትናንት እሁድ ከአምስት ሀገራት መሪዎች ጋር በእስራኤል እና ሐማስ መካከል በሚካሄደው ጦርነት ላይ ተነጋግረዋል።

ባይደን እና የእንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሣይ እና ጀርመን መሪዎች በጋራ በስልክ ከተወያዩ በኋላ ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ ለእስራኤል እና ራሷን የመከላከል መብቷ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

እስራኤል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕጎችን እንድታከብር እና በጋዛ የሚገኙ ሲቪሎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጥንቃቄ እንድታደርግ ጠይቀዋል። ባለፈው ዓርብ ሁለት ታግተው የነበሩ አሜሪካውያን መለቀቃቸውን እና የሰብዓዊ ርዳታም ቅዳሜ ዕለት መግባት መጀመሩን መሪዎቹ በመልካም ተቀብለውታል።

ግጭቱ ወደ ቀጠናው ሀገራት እንዳይዛመት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚያደርጉ እና በምካከለኛው ምስራቅ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።

ፕሬዘደንት ባይደን በተጨማሪም፣ የሰብዓዊ ርዳታ ወደ ጋዛ መግባቱን በመልካም እንደተመለከቱት ትናንት እሁድ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ በስልክ ገልጸውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች የሰብዓዊ ርዳታው ቀጣይነት ያለው እንደሚሆን አረጋግጠዋል ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG