በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን አስተዳደር መሣሪያ ሻጮች የገዢዎችን ዳራ እንዲያጣሩ አዘዘ


 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

በአሜሪካ መሣሪያን በሱቅም ሆነ በአውደ ርዕይ ላይ የሚሸጡ ነጋዴዎች፣ የገዢዎችን የኋላ ታሪክ እንዲያጣሩ የባይደን አስተዳደር ደንብ አውጥቷል።

በሺሕ የሚቆጠሩ የመሣሪያ ነጋዴዎች፣ ደንቡን በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።

ደንቡ፤ ባልተፈቀደላቸውና የገዢዎችን ዳራ በማያጣሩ ነጋዴዎች በየዓመቱ በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ መሣሪያዎች የሚሸጡበትን ሁኔታ እንደሚያስቀር ይታመናል።

በመሣሪያ የሚፈፀም ጥቃትና ሁከትን ለማስቆም አስተዳደሩ በቅርቡ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ እንደሆነም ተነግሯል።

አስተዳደራቸው ሕይወት በከንቱ እንዳይጠፋ አስፈላጊውን ሁሉ እንዳሚያደርግ የገለጹት ጆ ባይደን፣ የአሜሪካ ም/ቤት በመላ ሃገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆንና የገዢዎችን የኋላ ታሪክ እንዲጣራ የሚያስገድድ ሕግ እንዲያወጣ ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG