በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከህጻናት ወተት አምራች ኩባኒያዎች መሪዎች ጋር ተወያዩ


ፕሬዚዳንት ባይደን ከህጻናት ወተት አምራች ኩባኒያዎች መሪዎች ጋር ተወያዩ
ፕሬዚዳንት ባይደን ከህጻናት ወተት አምራች ኩባኒያዎች መሪዎች ጋር ተወያዩ

ቤቢ ፎርሚዩላ የሚባለውን ለህጻናት የሚሆን አልሚ ምግብ የያዘ ወተት አምራቾች ጋር የተነጋገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠረው እጥረት ቤተሰቦችን እያስጨነቀ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አስተዳደራቸው ከውጭ አቅርቦቶችን በማስገባት በሀገር ውስጥ ምርቱን ለማፋጠን ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከገርበር እና ከሌሎች ሦስት አምራች ኩባኒያዎች አምራቾች ጋር ስብሰባ አድርገው ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን “ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማቅረብ ካለመቻል የበለጠ ቤተሰብን የሚያስጨንቅ ነገር የለም፡፡ አቅርቦቱ እንዲጨምር አስተዳደሬ የተቻለውን ሁሉ አንዲያደርግ መመሪያ የሰጠሁት በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ተዘግተው የቆዩት የፎርሙላ ወተቱ አምራቾች በተቻለ መጠን በፍጥነት ተከፍተው በብዛት የሚያመርቱበትን እና አሜሪካውያን ቤተሰቦች ወተቱን በተሻለ ዋጋ የሚያገኙበትን መንገድ ከኩባኒያዎቹ ጋር ሆነው እንዲፈልጉ መመሪያ ሰጥቻለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

የባይደን አስተዳደር ቤተሰቦች ለልጆቻቸው የሚያስፈልገውን ምግብ አግኝተው እንዲረጋጉ “ኦፐሬሽን ፍላይ ቤቢ ፎርሙላ “ብሎ በሰየመው እንቅስቃሴ ብዛት ያላቸው ዓለም አቀፍ አቅራቢዎች ለህጻናት ወሳኝ የሆኑ አቅርቦቶችን ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመላክ ፈቃድ ጠይቀዋል፡፡

ከብሪታንያ ሁለት ሚሊዮን ብልቃጥ የተላከ ሲሆን የአውስትሬሊያ ኩባኒያዎችም ተጨማሪ አቅርቦት ለመላክ እየተዘጋጁ ናቸው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት የምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር አስተዳደርን አበት ኩባኒያ የሚሽጋን ፋብሪካውን እንዲዘጋ ላደረገው እና የህጻናት ምግብ እጥረቱን ለቀሰቀሰው ችግር ፈጥኖ መፍትሄ አልፈለገም በማለት ወቅሰውታል፡፡ ፋብሪካው ተከነገ ወዲያ ቅዳሜ ይከፈታል ተብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG