በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከኑክሌር ጦር መሣሪያ ግንባታ ከሚያግደው ዓለምቀፍ ሥምምነት ወጣች


ማይክ ፖምፔዮ
ማይክ ፖምፔዮ

ዩናይትድ ስቴትስ ከአሥርት ዓመታት በላይ ከቆየው ሁሉንም ዓይነት የኑክሌር ጦር መሣሪያ ግንባታ ከሚያግደው ዓለምቀፍ ሥምምነት መውጣቷን ዛሬ አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ዕርምጃ በአንዳንድ ተንታኞች ዘንድ አዲስ የጦር መሣሪያ ግንባታ እሽቅድድም ይጭራል የሚል ሥጋት አሳድሯል።

ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ ከቀዝቃዛው ጦርነት ፍፃሜ ጀምሮ ብዙ ርቀት የሚጓዙ የኑክሌር ጦር መሣሪያዎችን ላለማምረት ከደረሱበት ሥምምነት - ዋሺንግተን ከነገ ቅዳሜ ጥር 25 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ራሷን ታገላለች ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ አስታውቀዋል።

ሩሲያ አንዳንድ ከ5 ሺህ ኪሎ ሜትሮች በላይ የሚጓዙ ከየብስ የሚተኮሱ ክሩዝ ሚሳይሎችን አስመልክቶ የተደረሱ ሥምምነቶችን ጥሳለች ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ትከሳለች። በተገቢው መንገድ ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት አለብን ብለዋል - ማይክ ፖምፔዮ፤ሞስኩ ክሱን አትቀበልም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG