በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር በስደተኞች ሁኔታ


የትረምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ድንበር የሚገቡ የውጭ ሀገር ሰዎች ጥገኝነት እንዳይጠይቁ ለመከልከል እየተንቀሳቀሰ ነው።

ዕርምጃው በአብዛኛው የሚጎዳው በሜክሲኮ በኩል የሚገቡ የማዕከላዊ አሜሪካ ሰዎችን ነው።

አስተዳደሩ ይፋ ባደረገው በዚህ ዕርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ እና የሀገር ደኅንነት ሚኒስቴሮች ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች ዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ ሰዎች ጥገኝነት በሚሰጥ ሌላ ሀገር በኩል በየብስ አቋርጠው ወደ አሜሪካ ከገቡ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ማመልከት አይችሉም።

ይህ የተገለፀው ትናንት ሰኞ ይፋ በተደረገው ባለ ሃምሳ ሥምንት ገጽ የፌዴራል መንግሥት ሰነድ ሲሆን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዊሊያም ባር ሲናገሩ በዩናይትድ ስቴትስ እና በሜክሲኮ ወሰን በኩል የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁጥር በከፍተኛ አሃዝ መጨመሩንና ከነዚያ ውስጥ ጥገኘነት ሊያገኙ የሚችሉት ጥቂት ናቸው ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG