በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒጀር የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት በፕሬዚዳንት ትራምፕ ማዘኗን ገለጸች

In this frame from video, Myeshia Johnson cries over the casket in Miami, Florida, Oct. 17, 2017, of her husband, Sgt. La David Johnson, who was killed in an ambush in Niger.
In this frame from video, Myeshia Johnson cries over the casket in Miami, Florida, Oct. 17, 2017, of her husband, Sgt. La David Johnson, who was killed in an ambush in Niger.

በያዝነው ወር ለኒጀር ውስጥ የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት የሟቹን ባለቤትዋን ስም “ላ ዴቪድ ጆንሰንን ለማስታወስ ሲንተባተቡ በመስማቴ የባሰ እንዳልቀስ አድርጎኛል” ስትል ዛሬ ተናግራለች።

በያዝነው ወር ኒጀር ውስጥ የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት የሟቹን ባለቤትዋን ስም “ላ ዴቪድ ጆንሰንን ለማስታወስ ሲንተባተቡ በመስማቴ የባሰ እንዳልቀስ አድርጎኛል” ስትል ዛሬ ተናግራለች።

በኒጀር የተገደለው አሜሩካዊ ወታደር ባለቤት በፕሬዚዳንት ትራምፕ ማዘኗን ገለጸች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:13 0:00

ሚየሽያ ጆንሰን /ABC/ በተባለው የአሜሪካ ቴሊቪዥን ቀርባ ዛሬ ስትናገር

“ከሁሉም ያሳዘነኝ ነገር ባለቤቴ እዛ የሄደው ለሀገራችን ለመዋጋትና ህይወቱን ለሀገራችን ለመስጠት ሆኖ ሳለ እንዴት ስሙን ማስታወስ ያቅታል? ባለቤቴ መልካም ወታደር የነበረ በመሆኑም ስሙን እንኳን ለማስታወስ አለመቻላቸው የባሰ አሳዝኖኛል። የባሰ እንዳለቅሰም አድርጎኛል ስትል” ሚየሽያ ጆንሰን ሃዘንዋን ገልጻለች።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ በበኩላቸው ከሁለት ሰዓታት በኋላ የራሳቸውን ምላሽ በትዊተር ሰጥተዋል። “ከአምሳ አለቃ ላ ዴቪድ ጆንሰን ባለቤት ጋር አክብሮት የተመላበት አነጋገር ተለዋውጠናል። የላ ዴቪድ ጆንሰን ስምንም ከመጀመርያውንም ካለምንም ማመንታት ነበር የጠራሁት” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG