በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩዲ ጁሊያኒ ለተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የግል ጠበቃ የነበሩት ሩዲ ጁሊያኒ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የግል ጠበቃ የነበሩት ሩዲ ጁሊያኒ

የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የግል ጠበቃ የነበሩት ሩዲ ጁሊያኒ እና ሌሎች 10 ተከሳሾች በአሪዞና ግዛት በፕሬዝደንት ጆ ባይደን አሸናፊነት የተጠናቀቀውን የ2020 ዓ/ም የአሜሪካ ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ሞክረዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን አስታውቀዋል።

የፍርድ ቤት መጥሪያን ላለመቀበል ለሳምንታት ሲሞክሩና በማኅበራዊ ሚዲያ አቃቢያነ ሕግ ላይ ሲያፌዙ የነበሩት ጁሊያኒ፣ የ10ሺሕ ዶላር ዋስትና እንዲያሲዙ ታዘዋል።

ጁሊያኒ ባለፈው ዓርብ በፍሎሪዳ 80ኛ የልደት ቀናቸውን በማክበር ላይ ሳሉ የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ተሰጥቷቸዋል።

ጁሊያኒ ምርጫ ተጭበርብሯል የሚል የሃሰት ወሬ በማሰራጨት እና የምርጫ ባለሥልጣናት ውጤቱን እንዲቀይሩ በመገፋፋት የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

በተጨማሪም በአሪዞናም ሆነ በሌሎች ግዛቶች የሚገኙ የሪፕብሊካን ፓርቲ የምርጫ ባለሥልጣናት፣ ትረምፕ አሸናፊ እንደሆኑ እንዲያውጁ አበረታተዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

በአሪዞና በድምሩ 18 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሥርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG