በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለጀርመን ከስምንት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሂሊኮፕተሮችን ሽያጭ አጸደቀች

የባይደን አስተዳደር፣ የኔቶ አጋር ለኾነችው ጀርመን፣ ቺኑክ የተሰኙ ሂሊኮፕተሮች የ8ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ፣ ትላንት ኀሙስ አጸድቋል፡፡
የባይደን አስተዳደር፣ የኔቶ አጋር ለኾነችው ጀርመን፣ ቺኑክ የተሰኙ ሂሊኮፕተሮች የ8ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ፣ ትላንት ኀሙስ አጸድቋል፡፡

የባይደን አስተዳደር፣ የኔቶ አጋር ለኾነችው ጀርመን፣ ቺኑክ የተሰኙ ሂሊኮፕተሮች የ8ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሽያጭ፣ ትላንት ኀሙስ አጸድቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አሜሪካ ለጀርመን 60 ቺኑክ ሂሊኮፕተሮችን፣ የሚሳየል ጥቃት ማንቂያዎችን፣ ከሞተሮች እና መለዋወጫዎቻቸው ጋራ እንደምትሸጥላት፣ ለምክር ቤቱ አስቀድሞ ማስታወቁን አመልክቷል፡፡

ቺኑክ፣ ከሠራዊቱ ሂሊኮፕተሮች ላቂያ ያለው እንደኾነ የጠቀሰው የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባ፣ ሂሊኮፕተሩ፥ ወታደሮችንና መሣሪያዎችን ለማጓጓዝ ያገለገለና፣ በአፍጋኒስታንና በኢራቅ ዐውደ ውጊያዎች የታወቀ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ይኸው ሂሊኮፕተር፣ ባለፈው ሚያዝያ ወር፣ በሱዳን የነበሩ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሠራተኞችን ለማውጣት ማገለገሉም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

የሂሊኮፕተሮቹ ሽያጭ፣ ጠንካራውን የጀርመን ወታደራዊ ዐቅም ይበልጥ የሚያሳድገው ሲኾን፣ “አካባቢያዊ ስጋቶችን ይከላከላል፤” ሲል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ጀርመን የሸመተቻቸው የአሜሪካ ሂሊኮፕተሮች፣ በዩክሬን ጥቅም ላይ እንዲውሉ የታሰቡ አለመኾናቸው ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ፣ የሽያጭ ዕቅዱ፣ በአውሮፓ ለፖለቲካ እና ኢኮኖሚ መረጋጋት አስፈላጊ እና ኃያል አጋር የኾነውን የኔቶን ደኅንነት በማሻሻል፣ የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ እና ብሔራዊ ደኅንነት እንደሚደግፍ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG