በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰበር ዜና የፕሬዚዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ ዕገዳ ፀና


በአመዛኙ ሙስሊም ከሆኑ ሰባት ሀገሮች ፍልሰተኞችና ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥለውት የነበረውን የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ ያስቆመው የሴአትል ዳኛ ውሣኔ በይግባኝ ሰሚ ችሎት ፀና፡፡

የካሊፎርኒያዪቱ ግዙፍ ከተማ ሳን ፍራንሲስኮ ላይ የተሰየመው ዘጠነኛው አካባቢያዊ (የወረዳ)ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሳለፈው ውሣኔ ቀደም ሲል የፕሬዚዳንት ትራምፕ ዕገዳ ለጊዜው እንዲታገድ የዋሺንግተን ግዛት ዋና ከተማ ሲያትል ተቀማጭ የሆኑት ፌደራል ዳኛ ጄምስ ሮባርት ሰሞኑን አዝዘው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሦስት ዳኞች የተሰየሙበት የሳን ፍራንሲስኮው ችሎት የተሟጋቾቹን ወገኖች እሰጥ-አገባ ዛሬ ካዳመጠ በኋላ ነው የበታች ፍርድ ቤቱ ውሣኔ እንዲፀና በሙሉ ድምፅ የወሰነው፡፡
ጉዳዩ ለመጨረሻ ውሣኔ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሳይሄድ እንደማይቀር ተነግሯል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG