በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በ10 የሐማስ አባላት እና የገንዘብ ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጣለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በማድረስ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎችን ለገደለው ሐማስ ምላሽ ለመስጠት፣ በ10 የሐማስ ቡድን አባላት እና የፍልስጥኤም ታጣቂ ድርጅት የፋይናንስ መረብ ላይ ማዕቀብ እንደጣለች አስታውቃለች።

በገንዘብ ሚኒስቴር አማካይነት፣ ዛሬ ረቡዕ በወጣው የማዕቀብ ርምጃ ዒላማ የተደረጉት፥ የሐማስን የኢንቨስትመንት ይዞታ የሚያስተዳድሩ አባላት፣ ከኢራን አገዛዝ ጋራ የቅርብ ትስስር ያለውና መሠረቱን በኳታር ያደረገ የፋይናንስ አስተባባሪ፣ ቁልፍ የሐማስ አዛዥ፣ እንዲሁም በጋዛ የዲጂታል የምንዛሬ ለውጥ አገልግሎት ሰጭ እንደኾኑ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት ዬለን፣ “ዩናይትድ ስቴትስ የሐማስ ገንዘብ ለጋሾችንና አስተባባሪዎችን ለማጥቃት፣ ወሳኝ ርምጃ እየወሰደች ነው፤” ማለታቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

“የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ መሪ፥ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን፣ በእስራኤል ላይ የተፈጸመው ጥቃት፣ በጋዛ ለደረሰው ቀውስ እና መዘጋት ምላሽ ነው፤” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG