በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ7 የሩስያ የሥለላ መኮንኖች ላይ የወንጀል ክስ ተመሰረተ

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ በሰባት የሩስያ የሥለላ መኮንኖች ላይ የወንጀል ክስ መስርቷል። የሩስያን የኬሚካል መሳርያ መጠቀምን የሚመረመሩ ድርጅቶችና ፀረ ጉልበት ሰጪ መድሀኒት ባለሥልጣኖች የኮምፒተሮች መረቦችን ለመሰርሰር ሞክረዋል በሚል ነው የተከሰሱት።

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ በሰባት የሩስያ የሥለላ መኮንኖች ላይ የወንጀል ክስ መስርቷል። የሩስያን የኬሚካል መሳርያ መጠቀምን የሚመረመሩ ድርጅቶችና ፀረ ጉልበት ሰጪ መድሀኒት ባለሥልጣኖች የኮምፒተሮች መረቦችን ለመሰርሰር ሞክረዋል በሚል ነው የተከሰሱት።

ስለ ክሱ ያስታወቁት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጆን ደመርስ ሩስያውያኑ /GRU/ በሚል አህጽሮት የሚታወቀው የሩስያ ወታደራዊ የሥለላ ድርጅት ሰራተኞች ናቸው ብለዋል።

የዳች ባለሥልጣኖች በበኩላቸው አራት የ/GRU/ መኮንኖችን እንዳባረሩ ዛሬ አስታውቀዋል። የኬሚካል መሳርያ ዕገዳን ለማስከበር የኬሚካል መሳርያ ተከታታይ ድርጅት አጠገብ የሥለላ መሳርያ ይዘው በመገኘታቸው እንደተባረሩ ባለሥልጣኖቹ ጠቁመዋል።

ብሪታንያና አውስትራልያም የሩስያ ሰላዮች ፀረ ዓለምቀፍ ጉልበት ሰጪ መድሀኒት አገልግሎትንና ከአቻ አምና የተካሄደውን የአሜሪካ ምርጫን ዒላማ ያደረገ የሳይበር ሥርሰራ ተግባር ፈፅመዋል በሚል ሩስያን ከሰዋል።

የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሱን በማስተባበል “የፈጠራ ክሶች ናቸው” ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG