በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለሱዳንና ጎረቤት አገራት ተጨማሪ 172 ሚሊዮን ዶላር መደበች


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ዩናይትድ ስቴትስ ለሱዳን እና አጎራባች አገራት ተጨማሪ 172 ሚሊዮን ዶላር እንደምሰጥ ትናንት ማክሰኞ አስታውቃለች፡፡ ገንዘቡ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ለተጠፈረው ሰብአዊ ቀውስ ምላሽ የሚውል ነው ተብሏል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ባወጡት የጽሁፍ መልዕክት አገራቸው እስከአሁን 500 ሚሊዮን ዶላር ለሱዳን እና አካባቢ አገራት እንደላከች፤ ገንዘቡም ለፍልሰተኞች፣ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና በአጠቃላይ በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ሰለባ ለሆኑት እንደሚውል ጠቁመዋል።

ከሱዳን ሌላ ርዳታው የሚመለከታቸው አገራት ቻድ፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን እና መካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ ናቸው።

በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተላለፈ ጥሪ፣ ለሱዳን 1.5 ቢሊዮን ዶላር መሰባሰቡን፣ ድርጅቱ ሰኞ ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG