በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የአጎላውን ፕሬዝደንት ተቀብለው አነጋገሩ


ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ የአንጎላውን ፕሬዝደንት ዡዋ ሎሬንሶ
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ የአንጎላውን ፕሬዝደንት ዡዋ ሎሬንሶ

ፕሬዝደንት ጆ ባይደን፣ የአንጎላውን ፕሬዝደንት ዡዋ ሎሬንሶ በትናንትናው ዕለት በዋይት ሃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸው በአብዛኛው ያተኮረው፣ ከአሜሪካ በሚሰጠው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባውና፣ በነዳጅ ሐብት የበለፀገችውን አገር ወደቦች ከአህጉሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ጋር በሚያገናኘው የባቡር መንገድ ላይ መሆኑ ተነግሯል።

የዋይት ሃውሱ ሥነ ስርዓት፣ ሁለት በመካሄድ ያሉ ጦርነቶች የአስተዳደራቸውን በርካታ ግዜ በመውሰድ ላይ እያሉ ባለበት ወቅትም፣ ለአፍሪካ ትኩረት እንደሚሰጡ ያመላከተ መሆኑን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

የዋይት ሃውስ ጉብኝቱ፤ በዡዋ ሎሬንሶ አስተዳደር ዘመን፣ አንጎላ ከቻይና እና ሩሲያ ላይ ፊቷን አዙራ የአሜሪካ አጋር በመሆን የአቋም ለውጥ ባደረገችበት ወቅት የተካሄደ ነው ተብሏል። ባይደን በዚህ ዓመት አፍሪካን እንደሚጎበኙ ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን፣ ጉብኝቱ ላይካሄድ እንደሚችል በመነገር ላይ ነው። ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ግን በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ወደ አፍሪካ በርካታ ጉብኝቶችን አድርገዋል።

የሁለቱ መሪዎች በዋይት ሃውስ መገናኘት፣ በታሪካዊ ወቅት የተደረገ መሆኑን ባይደን ተናግረው፣ አሜሪካ በአፍሪካም ሆነ በአንጎላ ላይ ትኩረቷን እንደጣለች ገልፀዋል።

ሎሬንሶ በበኩላቸው፣ አገራቸው ከሜሪካ ጋር በኢኮኖሚ እና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG