በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የሕይወት አድን ድጋፍ እንዲፋጠን የአሜሪካ አምባሳደር አሳሰቡ


በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር

በትግራይ ክልል የሕይወት አድን ድጋፍ እንዲፋጠን ተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር አሳሰቡ።

ኢትዮጵያውያን እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ የበለጠ ሥራ መሰራት እንዳለበት ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ራይነር ተናግረዋል።

በሌላም በኩል የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንደሚያሳስባቸው የገለፁት አምባሳደሩ

"በፍጥነት እንዲያበቃም ጥሪ ማድረጋችንን እንቅጥላለን" ብለዋል።

ግድያዎችን ፣ የጾታ ጥቃቶችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ተጨባጭነት ያላቸው ሪፖርቶች ላይ በትግራይ እንደዚሁም መተከልን በመሳሰሉ ሌሎች ቦታዎች ገለልተኛ ማጣራት እንዲደረግም ጠይቀዋል።

ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ የማንኛውም መንግሥት መብትና ግዴታ ውጤት መሆኑን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።

የትግራዩ ጦርነት የተካሄደው የሃገሩን የግዛት አንድነትና የሕዝቦቹን ደሕንነት የመጠበቅ ግዴታ ባለበት የፌደራሉ መንግሥት እና ሕገ ወጥ በሆነ የትጥቅ አመጽ መካከል እንደሆነም አምባሳደሩ ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በትግራይ ክልል የሕይወት አድን ድጋፍ እንዲፋጠን የአሜሪካ አምባሳደር አሳሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:15 0:00


XS
SM
MD
LG