በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የአልሸባብ አባላት ተገደሉ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት አራት የፅንፈኛው አልሸባብ አባላት መግደሏን እና ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ አቅራቢያ ፈንጂ ጭኖ ይጓዝ የነበረ መኪና ማውደሟን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ አስታወቀ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት አራት የፅንፈኛው አልሸባብ አባላት መግደሏን እና ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ አቅራቢያ ፈንጂ ጭኖ ይጓዝ የነበረ መኪና ማውደሟን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ አስታወቀ፡፡

የአየር ጥቃቱ የተካሄደው ከሞቃዲሾ በስተምዕራብ ሃያ አምሥት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ ሲሆን መኪናው ላይ የተጫነው ፈንጂ፣ ሞቃዲሾ ውስጥ በሲቪሎች ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳት መከላከሉን ዕዙ አስታውቋል።

የአፍሪካ ዕዙ ባወጣው መግለጫ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር በማስተባበር በተካሄደው የአየር ጥቃት አንድም ሲቪል ሰው እንዳልተገደለ አውቀናል ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ በሽብርተኛው አልሸባብ እና ቁጥራቸው እየጨመረ በመጣው ከእስላማዊ መንግሥት ቡድን ጋር የተቆራኙ ተዋጊዎች ላይ ከሠላሣ በላይ መሰል የአየር ጥቃቶች አድርሳለች።

ዕሁድ ዕለት ደቡባዊ ሶማሊያ ውስጥ በተካሄደ የአየር ጥቃት ኪስማዮ አቅራቢያ አሥራ ሦስት የአልሸባብ ተዋጊዎች መገደላቸው የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG