በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ዘጠኝ የአል ሸባብ ሚሊሻዎች መግደሉን ገለፀ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል በደቡባዊ ሶማልያ በከፈተው ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ የአል ሸባብ ሚሊሻዎች መግደሉን ገልጿል። ጥቃቱ የተከፈተው በመንግሥት ኃይሎች ላይ የአማፅያን ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ነው ተብሏል።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል በደቡባዊ ሶማልያ በከፈተው ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ የአል ሸባብ ሚሊሻዎች መግደሉን ገልጿል። ጥቃቱ የተከፈተው በመንግሥት ኃይሎች ላይ የአማፅያን ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ነው ተብሏል።

አፍሪካ ኮማንድ የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ዕዝ በገለፀው መሰረት ቢያንስ አንድ የአል ሸባብ አማፂ በአየር ጥቃቱ ቆስሏል። ጥቃቱ ትላንት የተከፈተው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በመተባበር ነው። ኪስማዩ ከተባለችው ደቡባዊት ከተማ 40 ኪሎሜትር ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ ነው የአየር ድብዳባው የተካሄደው።

የተገደሉም ሆነ የቆስሉ ሲቪሎች አለመኖራቸውን ነው ዛሬ የገመገምነው ብሏል መግለጫው።

ዩናይትድ ስቴትስ ካለፈው ጥር ወር አንስቶ ሶማልያ ላይ ከ20 በላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ፈፅማለች።

ከአል ቃይዳ ጋር የተሳሰረው አል ሸባብ የሶማልያን መንግሥት ገልብጦ አክራሪ እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት ውጊያ ከጀመረ 22 ዓመታት ሆኖታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG