በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የአል-ሻባብ ታጣቂዎችን ገደለች


ዩናይትድ ስቴትስ ሶማሊያ ውስጥ በአል-ሻባብ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት አስራ አራት ታጣቂዎች መገደላቸውን የማዕከላዊ ሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የአየር የተካሄደው በአል-ሻባብ ላይ ጥቃት ለከፈቱ የሶማሊያ ወታደሮች ድጋፍ ለመስጠት መሆኑን ቪኦኤ በስልክ ያነጋገራቸው ወታደራዊ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

የሶማሊያ የጦር ኃይል በአካባቢው የቡድኑን ምሽጎች ሙሉ በሙሉ መደምሰሱንና ጠንካራ ይዞታው የነበሩ አካባቢዎችን መያዙን አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ስለዚህ ድብደባ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል የአፍሪካ ዕዝ ባለፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫ ከኢትዮጵያ ጋር በሚዋሰነው የሶማልያ ሂራን ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ በለድዌይን አቅራቢያ የሶማሊያን ጦር ለማገዝ ባካሄደው የአየር ጥቃት አራት የአልሻባብ ተዋጊዎችን መግደሉን አስታውቆ ነበር።

XS
SM
MD
LG