በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ12 እስከ 15 ዓመት ልጆች ማጠናክሪያውን ክትባት መውሰድ ይችላሉ ተባለ


የኮቪድ-19 የማጠናከሪያ ክትባት
የኮቪድ-19 የማጠናከሪያ ክትባት

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) ትናንት በሰጠው መግለጫ ዕድሜያቸው ከ12 እስከ 15 የሚደርሱ ታዳጊ ወጣቶች የፋይዘርና ባዮንቴክ የኮቪድ-19 የማጠናከሪያ ክትባትን መውሰድ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

ኤፍዲኤ ጨምሮ እንዳስታወቀው የመከላከል አቅማቸው ደካማ የሆነ ከ5 እስከ 11 ዓመት የሚደርሱ ህጻናትም የማጠናክሪያውን ክትባት መውሰድ እንደሚችሉ አመልክቷል፡፡

ክትባቶቹን መስጠት የተፈለገው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰፋፋ በመጣው የኦሚክሮን ቫይረስ ሳቢያ ትምህርት ቤቶች እንዳይዘጉ በመስጋት መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG