በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንግረስ አባላት የአፍሪካ ዴሞክራሲ ወደኋላ እየተጎተተ ነው ይላሉ


ፎቶ ፋይል : የዩናይትድ ስቴት ህግ አውጭ ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ን ኡስ ኮሚቴ ካረን ባስ
(July 1, 2019. Moki Kindzeka)
ፎቶ ፋይል : የዩናይትድ ስቴት ህግ አውጭ ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ን ኡስ ኮሚቴ ካረን ባስ (July 1, 2019. Moki Kindzeka)

የዩናይትድ ስቴት ህግ አውጭዎች፣ በከሰሃራ በታች ባሉ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች፣ ወደ ኋላ እየተንሸራተቱና እየተሸረሸሩ ሄደዋል ያልዋቸውን የዴሞክራሲና የዴሞክራሲ ተቋማት፣ በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት፣ እንዲሁም በጤና እና በትምህርት አቅርቦት ላይ የሚያስከትሏቸውን ችግርን ለመመርመር የተሰዩሙት የምክር ቤቱ የን ኡስ ኮሚቴ አባላት በትናንትናው እለት ተሰብስበው ነበር፡፡

የዩናይትድ ስቴት ህግ አውጭዎች፣ በከሰሃራ በታች ባሉ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች፣ ወደ ኋላ እየተንሸራተቱና እየተሸረሸሩ ሄደዋል ያልዋቸውን የዴሞክራሲና የዴሞክራሲ ተቋማት፣ በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት፣ እንዲሁም በጤና እና በትምህርት አቅርቦት ላይ የሚያስከትሏቸውን ችግርን ለመመርመር የተሰዩሙት የምክር ቤቱ የን ኡስ ኮሚቴ አባላት በትናንትናው እለት ተሰብስበው ነበር፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ማርያማ ዲያሎ የሚክተለውን ዘገባ አዘጋጅታለች ፡፡

ከሰሃራ በታች የሚገኙ የተለያዩ አፍሪካ አገሮች ከመሠረታዊ የዴሞክራሲ መርህ ርቀው፣ እንደገና ወደኋላ እያፈገፈጉ ነው የሚሉት በዩናይትድ ስቴት ህግ አውጭ ምክር ቤት፣ የአፍሪካ ጉዳዮች እንዲሁም፣ የዓለም የጤና፣ ሰብአዊ መብት ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ ካረን ባስ ናቸው፡፡ ስለ ወቅቱ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሁኔታ እንዲህ ብለዋል::

ዴሞክራሲያዊ ሂደቶችን ወደ ኋላ የመጎተቱ ነገር ነጻና ፍትሃዊ ምርጫዎችን ባለማድረግ ብቻ ሳይሆን የንንግርን ነጻነትን መጣስ፣ መንግሥትን የሚያቀወሙና ተጠያቂ እንዲሆን የሚያደርጉ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ማፈንና ማሰናከል የህግ የበላይነትን ማዳካም የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡

ትናንት ረቡዕ በተካሄደ፣ የህዝብ አስተያየት መቀበያ መድረክ ላይ ባስ እንዳሉት ሥልጣን ላይ መቆየት በሚፈልጉት መሪዎች በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች የምርጫ ህጎችን መለወጥ፣ ነጻነትን እየገደቡና በማለት እንዲህ ብለዋል፡፡

“እጅግ በጣም የሚያሳስበው በታንዛንያ ያለው ሁኔታ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ በቅርቡ ያስተዋወቅኩት ውሳኔ 1120 ይህኑን የሚመለከት ነው ፡፡ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ተቃዋሚዎችን እያፈነ መሠረታዊ የንግግርና የመሰብሰብ ነጻነትን እየገደበ ሥልጣን ለመቆየት በግልጽ እየሠራ ነው፡፡ በኮትዲቯርም ተመሳሳይ ሁኔታዎችን እየተመለከተን ነው፡፡ አስፈጻሚው አካል ዴሞክራሲን የሚያዳክሙ ተቋማትን ህጋዊ እያደረገና ለነሱም የተመቹ ጸረ ዴሞክራሲዊ ህግጋትን እያወጣ ነው፡፡”

ኮትዲቯር ውስጥ በቅርቡ በተካሄደው አመጽ ካልፈው ወር ጀምሮ እስካሁን ከአስር በላይ ሰዎች ሞተዋል፡፡ የ78 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት አልሳኔ ኡታራ በዚህ ዓመት በምርጫው ላለመወዳደር የገቡትን ቃል አጥፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እሳቸው እንዲተኩ በግል የመረጧቸው ሰው በድንግተኛ የልብ ህመም ባለፈው ሀምሌ ያረፉ በመሆናቸው እንደገና ራሳቸው ተመልሰው ቦታውን በመያዝ የፓርቲያቸው እጩ ሆነው ለምርጫው ቀርበዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴት ምክር ቤት ቀርበው ምስክርነታቸው የሰጡት ባለሙያዎች ወደኋላ እየተንሸራተተ የሄደውን የዴሞክራሲ ሂደት የፈጠረባቸውን ስጋት ገልጠዋል፡፤ ከብሄራዊ ዴሞክራሲ ተቋም የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተወካይ ክርስቶፈር ፋሙናዩ ለምክር ቤቱ እንዳስታውቁት እኤ አ በ1989 ከነበሩት የአፍሪካ አገሮች ውስት የዴሞክራቲክ ነጻነት አለባቸው የተባሉት ሁለት አገሮች ብቻ ናቸው፡፡

ከ20 ዓመታት በኋላ ሁለት ሶስተኛዎቹ ነጻ ወይም በከፊል ነጻ ተብለው የተመደቡ ቢሆንም አሁን ግን እነዚያ የተመዘገቡ መሻሻሎችም መልሰው እየጠፉ ነው፡፡

ክርስቶፈር ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገሩ} “ቀደም ሲል እንደ ጥሩ ምሳሌ ተደርጎ ተወስዶ የነበረው የምዕራብ አፍሪካ ሁኔታም ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ነው፡፡ ማሊ ከባድ መፈንቅለ መንግሥት አጋጥሟት የነበረ ሲሆን በጊኒ ኮናክፍሪ እንዳ ኮቲድቯርም ውስጥ በሚካሄዱት ምርጫዎች እንደገና ለመወዳደር በሚፈልጉት መሪዎች ሳቢያ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቷል፡፡ በመካከለኛው የአፍሪካ ቀጠና አሁንም በዓለም ለረጅም ጊዜ አገዛዝና ሥልጣን ላይ በቆዩ ሶስቱ መሪዎች እንደተያዘ ነው፡፡”

ክርስቶፈር እንደሚሉት አሁንም ሥልጣን ላይ ያሉና ረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ በመቆየት ከሚጠቀሱ መሪዎች መካከል የኢኳቶሪያል ጊኒ መሪ 41 ዓመት፣ የካሜሩን 58 ዓመት ሲሆኑ የኮንጎ ብራዛሊም አራት አስርት ዓመታት እየተጠጋቸው ነው፡፡ ነጻነትና ዲሞክራሲን እያጣጣሙ ያሉ የአፍሪካ አገርች በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ከሰሃራ በታች ነጻነት ባለበታ አገር ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካውን 9 ከመቶ ብቻ ናቸው፡፡በፍሪደም ሀውስ፣ የአፍሪካ ነጻነት ጉዳዮች ፕሮግራም ድርጅት ድሬክተር የሆኑ ጃን ቴምን እንደሚሉት በቅርቡ በወጣው ሪፖርት መሠረት በዓለም ላይ የዴሞክራሲ ሥር ዐታቸው እያጡ ያሉ ወይም ዴሞክራሲ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነበሳቸው ካሉ አገሮች ውስጥ 12 የሚገኙ ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮች ነው፡፡ አንዳንዶቹ ክርስቶፈር እንደሚክተለው ይገልጿቸዋል፤

“ወደ ኋላ እየተንሸራተተ የሚሄደው ዴሞክራሲ የሚያመጣው ሸክም በዜጎች ጫንቃ ላይ ይወድቃል፡፡ ለምሳሌ በጊኒና እና ካሜሩን መንግሥትን በሰላማዊ መንገድ የሚቃወሙ ሰዎች ይጠቃሉ፡፡ በኢትዮጵያና በቻድ ያሉት ደግሞ መንግሥት ኢንተርኔቱን መዝጋት በፈለገ ቁጥር ፈጽሞ መጠቀም አይችሉም፡፡ የሲቪል ማህበራትና ቡድኖች እንቅስቃሴዎች በታንዛኒያና ብሩንዲ ከፍተኛ ገደብ ተጥሎባቸዋል፡፡ በናይጄሪያና ዚምባቡዬ ጋዜጠኞች እስርና ማስፈራሪያ ይደርሳቸዋል፡፡”

ምርጫን በሚመለከት በርግጥ ተስፋ የሚሰጡ አንዳንድ ምልክቶች እንዳሉ ደግሞ የሚናገሩ የመካለከያ ተቋማት ተንታኝና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ዶሪና ኤ ቤኮ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“የኬኒያ ሲቪል ማህበረሰብ ዜጎች፣ ማጭበርበር፣ ማስፈራራትና የመሳሰሉ ጥቃትና ችግሮችን ሲመለከቱ፣ እየቀረጹ የሚልኩባቸው መንገዶችን ፈጥረዋል፡፡ እነሱ የጀመሩትንም ብዙ የአፍሪካ አገሮች ይጠቁመባታል፡፡ በምርጫ ወቅትም በዚያ መንገድ የሚመጡ መረጃዎች በማዕክል የሚጠናቀሩበት ክፍል የነበረ ሲሆን፣ በዚያ ምክንያት የረገቡ ብዙ ውጥረቶችም ነበሩ፡፡ ተያይዘው የተዘረጉት፣ የጎንዮሽ ትይዩ የድምጽ አሰጣጣጥችም ፣ በይፋ የሚሰጡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶችን ትክክለኝነት ለመቆጣጠር ረድተዋል፡፡”

በአፍሪካ በተለይም በጋና ፣ሴነጋል፣ ሞሪሸ ቦትስ ዋና እና ደቡብ አፍሪካ፣ ተመሳሳይ የሆኑ ተስፋ ሰጭ ሁኔታዎች መኖራቸውን ዶ/ር ዶሪና ተናግረዋል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ማርያማ ዲያሎ ያዘጋቸው ዘገባ ነው፡፡)

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)​

የኮንግረስ አባላት የአፍሪካ ዴሞክራሲ ወደኋላ እየተጎተተ ነው ይላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00


XS
SM
MD
LG