በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካውያን የሚሰደዱበት፣ ከመኖርያቸው የሚፈናቀሉበት ምክንያት


ኬረን ባስ
ኬረን ባስ

በዩናይትድ ስቴትስ የህግ መመሪያ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሜቴ ስለአፍሪካ፣ ስለ ዓለምቀፍ ጤና፣ ስለ ሰብአዊ መብትና ዓለምቀፍ ድርጅቶች የሚመለከተው ክፍል አዲስ ሊቀ መንበር አፍሪካውያን የሚሰደዱበትና ከመኖርያቸው የሚፈናቀሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ዲሞክራትዋ የካሊፎርኒያ ተወካይ የምክር ቤት አባል ኬረን ባስ ይህን ያሉት ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ነው።

ከምክንያቶቹ አንዱ ግጭት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም ለግጭቶቹ መፍትኄ ማግኘቱ አንዱ መልስ ይሆናል ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጀምስ ባቲ ገልፀዋል።

ከአየር ንብረት ቀውስ ጋር የተያያዘ ችግርም ለስደትና ለመፈናቀል ምክንያት እንደሚሆን ባስ ገልፀዋል።

የጥቁር አሜሪካውያን የምክር ቤት አባለት ቡድን ሊቀ መንበር የሆኑት ኬረን ባስ ዩናይትድ ስቴትስ ባሉት አፍሪካውያን ስደተኞች ላይ ያለው አያያዝ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

ከሶማልያ፣ ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳንና ከላይቤርያ የመጡ የተወሰኑ አፍሪካውያን በጊዚያዊ መልክ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲኖሩና እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸውል። ይሁንና በትረምፕ አስታዳደር ወቅት ችግር ላይ ሊወድቁ ይቻላሉ የሚል ሥጋት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG