በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ በአፍሪካ


የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን
የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን

ዩናይትድ ስቴትስ በዓለሙ ድርጅት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ አፍሪካ ውስጥ የምትጫወተውን ሚና እየመረመረች ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በዓለሙ ድርጅት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ አፍሪካ ውስጥ የምትጫወተውን ሚና እየመረመረች ነው። ብሄራዊ የፀጥታ አማካሪው ጆን ቦልተንና የመከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ውስጥ ያሏትን ወታደሮችና በአህጉሪቱ የመደበችውን በጀት ወደ ሌላ አካባቢ ለማዞር እየመከሩ ነው ተብሏል።

የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪው ጆን ቦልተን ትላንት ያስተዳደሩን አዲስ የአፍሪካ ፖሊሲ ሲያስተዋውቁ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከእንግዲህ በኋላ “የማይረባ፣ ስኬታማ ያልሆነና ተጠያቂነት የሌለው” ሲሉ ለገለፁት በአፍሪካ ለተባበሩት መንግሥታት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ ድጋፍ አትሰጥም ብለዋል።

በዓለም ዙሪያ ለተባበሩት መንግሥታት የሰላም ጥበቃ ተልዕኮ ከፍተኛውን የገንዘብ መዋጮ የምትከፍለው ዩናይትድ ስቴትስ ናት። ለ2010 – 2011ዓ.ም ለአንድ ዓመት ከተመደበው የ6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በጀት አንድ ሦስተኛውን የምትሸፍነው ዩናይትድ ስቴትስ ናት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG