በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከአፍሪካ የምታስገባውን የምግብ ሸቀጥ ልትጨምር ነው


የዩኤስኤይድ ምክትል አስተዳዳሪ ኢዛቤል ኮልማን
የዩኤስኤይድ ምክትል አስተዳዳሪ ኢዛቤል ኮልማን

ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ የምታስገባውን የምግብ ሸቀጥ ለመጨመር አዲስ ተነሳሽነት ዛሬ ረቡዕ ይፋ አድርጋለች፡፡ ዓሣና የባህር ውጤቶች፣ ለውዝና የቅባት እህሎች እንዲሁም ቅመማ ቅመሞች ይገኙበታል።

“ልዩ አፍሪካዊ ምግቦች” ተብለው የተገለጹትን ሸቀጦች በቀጣዩ 18 ወራት ወደ አሜሪካ ለማስገባት 300 ሚሊዮን ዶላር እንደተመደበ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (USAID) ‘የአፍሪካ ንግድ ክፍል’ የተሰኘው ቢሮ አትላንታ ላይ በተዘጋጀ የንግድ ትርዒት ላይ ይፋ አደርጓል። የአትላንታው የንግድ ትርዒት በተለይም በደቡብ አፍሪካ ላይ ያተኮረ እንደነበር ታውቋል።

በፕሮግራሙ በአነስተኛ አቅም የሚያመርቱ ገበሬዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። “በርካታ አገራት ወደ አሜሪካ ገበያ ለመዝለቅ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንሻለን” ሲሉ የዩኤስኤይድ ምክትል አስተዳዳሪ ኢዛቤል ኮልማን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

አሜሪካ የሚገኙ አስመጪዎች ከአፍሪካ በርከት ያሉ የምግብ ሸቀጦችን ማስገባት እንደሚሹ እንደገለጹላቸው ኮልማን አስታውቀዋል።

በአሜሪካ የሚገኘው የአፍሪካ ዳያስፖራ ፍላጎትንም ከግምት ያስገባ ተነሳሽነት እንደሆነም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG