በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በሶማሊያ የማረጋጋትና የድጋፍ ፕሮግራሞች በመካሄድ ላይ ናቸው” አፍሪኮም


በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጀኔራል ማይክል ላንግሊ
በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጀኔራል ማይክል ላንግሊ

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ኃይል በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ላይ ሃገሪቱን ለቆ ለመውጣታ እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የማረጋጋትና የድጋፍ ፕሮግራሞች እየተካሄዱ እንደሆነ በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ አስታውቀዋል።

ከሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃመድ እና ከወታደራዊ አዛዡ ሜጄር ጀኔራል ሼክ ሙሃይዲን አዶ ጋራ እንደተነጋገሩ ያስታወቁት በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ አዛዡ ጀኔራል ማይክል ላንግሊ፣ የአፍሪካ ኅብረት በታህሳስ ወር ለቆ ሲወጣ፣ ሶማሊያ የራሷን ደህንነት መጠበቅ እንደምትችል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ዛሬ በኢንተርኔት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት አዛዡ፣ በደቡብ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ የሚደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች አካባቢዎቹን ከነውጠኖች በማስለቀቅ ላይ ያተኮሩ እንደሆነ የሶማሊያ ባለሥልጣናት እንደነገሯቸው ጠቅሠዋል። ሌሎችን አካባቢዎች ደግሞ ለማረጋጋት እየተሠራ መሆኑን እንደተረዱም አስታውቀዋል።

በአል-ሻባብ እየታበጠች ያለችውን ሃገር ለማረጋጋት ሰፊ ተዋጽኦ ያለው ጦር እንዲሰማራ የተመድ የፀጥታው ም/ቤት ከሁለት ዓመት ከመንፈቅ በፊት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

“በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ልዑክ” የተሰኘው አዲሱ ልዑክ፣ የአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ለቆ እንደወጣ እንደሚተካ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG