በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንክን የአፍሪካ ጉብኝት


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን በጸጥታ እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ከነገ ሰኞ ጀምረው በኬንያ ፥ በናይጄሪያ እና በሴኔጋል ጉብኝት የሚያካሂዱ መሆኑን ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

ብሊንከን በናይጄሪያ ከፕሬዚደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጋር በዐለም አቀፍ የጤና ደህንነት ዙሪያ በትብብር መስራትን፥ የኤነርጂ ተደራሽነት እንዲሁም ጸጥታን በሚመለከቱ ጉዳዮች እንደሚወያዩ መግለጫው አመልክቷል፡፡

በኬንያ ጉብኝታቸው ከፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ከሌሎችም ባለስልጣናት ጋር ኢትዮጲያን፥ ሱዳንን እና ሶማሊያን የሚመለከቱ የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃ አባል ሃገርነታችን በምናተኩርባቸው የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንወያያለን ማለታቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡

በመጨረሻ በሚጎበኟት በሴኔጋል ደግሞ ከፕሬዚደንቱ ማኪ ሳል ጋር ዳካር ላይ በሚያደርጉት ውይይት የሁለቱን የቅርብ አጋርነት በድጋሚ እንደሚያረጋግጡላቸው ነው የስቴት ዲፓርትመንቱ መግለጫ ያመለከተው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ከነገ ሰኞ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ የሚዘልቀውን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን የሚያደርጉት ዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንዲያከትም በአፍሪካ ህብረት መሪነት የተያዘውን ጥረት ለማጠናከር እየተንቀሳቀሰች ባለችበት ባሁኑ ወቅት መሆኑን ዜናው ጨምሮ አመልክቷል።
አያይዞም በሀገሪቱ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ አንዳንድ የ ተ መ ድ እና የአፍሪካ ህብረት ሰራተኞችም ጭምር ያሉባቸው የትግራይ ተወላጆች እንደታሰሩ የሚገልጹ ሪፖርቶችን ተከትሉ ውጥረቱ ተባብሷል" ብሏል።

ከትናንት በስተያ ዐርብ በሰጡት ቃል "ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነው ሊያፈራርሳት የሚችል አደጋ እጅግ ያሳስበኛል" ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ወገኖች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጥረት እያደረጉ ካሉት ከአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጋር በቅርበት በመስራት ላይ እንደምትገኝ አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡኹሩ ኬኒያታ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማርፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG