በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋኒስታን አይሲስ ከፍተኛ አባላት መገደላቸውን አስታወቀች


FILE - In this Jan. 31, 2010, photo, an unmanned U.S. Predator drone flies over Kandahar Air Field, southern Afghanistan, on a moonlit night.
FILE - In this Jan. 31, 2010, photo, an unmanned U.S. Predator drone flies over Kandahar Air Field, southern Afghanistan, on a moonlit night.

አፍጋኒስታን ካቡል አውሮፕላን ጣቢያ መግቢያ ላይ የተፈጸመውን ብዙ ህይወት ያጠፋ ጥቃት ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፀፋ እርምጃ መውሰዱ ተዘገበ።

በዚሁ የአፀፋ ጥቃት ላይ የተሰማሩት ድሮኖች ከፍንዳታው ጀርባ አለ በሚሉት አፍጋኒስታን ውስጥ የአይሲስ ክንፍ መሆኑ በሚነገረው የኮራሳን እስላማዊ መንግሥት ወይም ኢስላሚክ ስቴት ኮራሳን በሚባለው ቡድን መሪ ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ ታውቋል።

የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ ሻምበል ቢል አርቤን ባወጡት መግለጫ ዒላማቸውን መግደላቸውን እና በሲቪሎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ እንደሚያውቁ አመልክተዋል። ማምሻውን በወጣ ሌላ መረጃ በአፀፋ ጥቃቱ ሁለት የቡድኑ መሪዎች እና የጥቃቱ አቀናባሪዎች መገደላቸው ተገልጿል።

አይሲስ ኬ170 አፍጋናውያን እና 13 የአሜሪካ ወታደሮች እንደተገደሉበት የተገለጸውን ጥቃት ማድረሱን አስታውቆ ኃላፊነት ወስዷል።

ሌሎች ጥቃቶችም በአይሮፕላን ጣቢያው ላይ ሊደርሱ ይችላሉ በሚል ጥርጣሬ ካቡል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ሁሉ ከአራቱም የጣቢያው መግቢያ በሮች አካባቢ እንዲርቁ አሳስቦ ነበር።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪም ትናንት በሰጡት መግለጫ "ሌላ ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ባለስልጣናቱ ያስባሉ" ብለው የነበረ ሲሆን የመከላከያ መስሪያ ቤቱ የፔንታጎን ቃል አቀባይ ጃን ከርቢም የታመኑ እና የታወቁ የተከታይ ጥቃት ሙከራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ጥቃቶቹን ለመመከት እና ለማክሸፍ ዝግጁ መሆናቸውን ከርቢ ቢናገሩም የተፈጠረው የፀጥታ ስጋት አሜሪካውያኑን እና አንዳንድ አፍጋናውያንን የማውጣቱን ጥረት አዳጋች እንዳደረገው ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ እንግሊዝ ሲቪሎችን ለማውጣት ታደርጋቸው የነበሩ በረራዎችን ማቋረጧን እና ወታደሮቿን እና ዲፕሎማቶቿን እየመለሰች መሆኗን ዛሬ አስታውቃለች። ፈረንሳይም ሲቪሎችን ከአፍጋኒስታን የማስወጣት እንቅስቃሴዋን ማቋረጧን ቀደም ሲል አስታውቃለች።

ይሁን እንጂ ሲቪሎችን የማስወጣቱ ሥራ ትናንት ሲጀመር ከአፍጋኒስታን ለመውጣት እየተጣደፉ ያሉ ቁጥራቸው የበዛ ሰዎች አይሮፕላን ጣቢያውን አጨናንቀውት ታይተዋል።

ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጃን ከርቢ በሰጡት መግለጫ በትናንቱ የአየር ጥቃት የአፍጋኒስታኑ የአይ ኤስ ክንፍ ሁለት ዋና ዋና መሪዎች ተገድለዋል። አንድ ሌላ አባል መቁሰሉን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG