በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የሩሲያ እና የዩክሬን ድርድር ውጤታማ እንደሚሆን የሚያሳይ ፍንጭ አላየሁም አለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ ዴሬክ ቾሌ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ ዴሬክ ቾሌ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ሦስተኛ ወሩን በያዘበት በዚህ ወቅት የሁለቱ ወገኖች ድርድር ፍሬያማ እንደሚሆን ብዙም ምልክት አላየንም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ተናገሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ ዴሬክ ቾሌ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ሩሲያውያኑ ትርጉም ባለው መንገድ ለመደራደር ፍቃደኝነቱ ያላቸው አይመስልም” ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ማክሰኞ እለት ሞስኮን ከጎበኙ በኋላ ወደኪየቭ የተጓዙ ሲሆን በሞስኮ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ለሁለት ሰዓት ያህል ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጉተሬዥን ወደሞስኮ አና ኪየቭ ከመጓዛቸው በፊት ያነጋገሯቸው መሆኑን የገለጹት ዴሬክ ሾሌ ወደሰላም የሚያመራ ሁኔታ ይኖር አንደሆን ከእርሳቸው ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን ብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ ቻይና ለሩሲያ ወረራ የምታደርገውን ድጋፍ በመፈተሽ የቀረበው ህግ ከትናንት በስተያ በተወካዮች ምክር ቤቱ በከፍተኛ ድምፅ አልፏል።

XS
SM
MD
LG