በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታይዋን ጉዳይ የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ጦርነት ገጽታዎችን የገመገመ አዲስ መጽሃፍ


የቻይና ታይዋን ካርታ
የቻይና ታይዋን ካርታ

ዋናው መቀመጫውን በዋሽንግተን ያደረገ አንድ ታዋቂ የፖሊሲ ጥናት ተቋም እንዳለው ቻይና ታይዋንን ከወረረች በሚል “የተሳሳሳተ ስሌት” ዩናይትድ ስቴትስ ሊቀሰቀስ ለሚችል ግጭት እየተዘጋጀች ነው ብሏል።

የአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲትዩት የተባለው ይህ የጥናት ተቋም “ለታይዋን መከታ ማበጀት” በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃው አዲስ መጽሃፍ ዋሽንግተን፣ ቻይና በታይዋን ላይ ወረራ የፈጸመች እንደሁ ሊቀሰቀስ የሚችለውን ጦርነት አጭር እና በዚያው ተገድቦ የሚካሄድ አድርጎ የማየት የሚል የተሳሳተ ትንበያ ነው የያዘችው ሲል ይከራከራል።

የተቋሙ አጥኝዎች እንደሚሉት ግን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር የፔንታጎን እቅድ “ረጅም ጊዜ ሊዘልቅ በሚችል ግጭት ዙሪያ የሚያተኩር መሆን አለበት።”

የአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የጥናት ባለሞያዎች ሃል ብራንድስ እና ማይክል ቤክሊ እንደተናገሩት ሊደርሱ ከሚችሉት እና እንደ አሳሳቢነት ከሚታዩ ሁኔታዎች በአንዱ ቤጂንግ የታይዋንን መከላከያ በሚሳይል መደብደብ ብቻ ሳይሆን፤ በምዕራብ ፓስፊክ ከሚገኙ ጥቂት ነገር ግን ግዙፍ የሆኑ የጦር ሰፈሮች የዩናይትድ ስቴትስ የባህር እና የአየር ኃይሎችም ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ። አክለውም በምዕራባዊ ፓስፊክ ሊቀሰቀስ የሚችል የዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና ግጭት ፈጥኖ አይበርድም ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ስታራምድ የቆየችው ፖሊሲ በታይዋን የባህር ወሽመጥ ወታደራዊ ግጭት እንዳይቀሰቀስ በብቃት ያስቀረች ሲሆን በአንጻሩ ጥቃት ቢቀሰቀስ ለሚያስፈልገው ስትዘጋጅ ቆይታለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቤጂንግ ታይዋንን አስመልክቶ እያሳየች ያለችው፣

"እያደረ እየጨመረ የመጣው ጠብ ቀስቃሽ ንግግር እና እንቅስቃሴ" ከፍተኛ ሥጋት እንዳሳደረባቸው አመልክተዋል።

ካሁን ቀደም ሲቪል መሪዎች የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሰራዊት ታይዋንን ከቻይና ጥቃት መከላከል የሚያስችል አዋጭ እቅዶች እንዲነድፉ ለጦር ባለሥልጣናት መመሪያ መስጠታቸውን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር የውስጥ ሰነድ አመልክቷል።

በቅርቡ፣ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቤጂንግ ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ ደጋግመው አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG