በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በሶሪያ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ለደረሰው የድሮን ጥቃት ኢራን አለችበት"


ፎቶ ፋይል፦ ድቡብ ሶሪያ በሚገኘው አልታንፍ የጦር ሰፈር የአሜሪካ ወታደሮች ስልጠና ሲሰጡ
ፎቶ ፋይል፦ ድቡብ ሶሪያ በሚገኘው አልታንፍ የጦር ሰፈር የአሜሪካ ወታደሮች ስልጠና ሲሰጡ

ኢራን፣ በድቡብ ሶሪያ በሚገኘው አል ታንፍ የጦር ሰፈር ባሉ፣ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ በደረሰው የድሮን ጥቃት፣ እጇ አለባት ተብሎ እንደሚታመን የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ ተናገሩ፡፡

ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ ባለሥልጣን፣ የኢራን ድሮኖች ለጥቃቱ ይዋሉ እንጂ፣ ድሮኖቹ ግን ከኢራን የተነሱ አይደሉም ብለዋል፡፡

በአምስት ድሮኖች የደረሰው ጥቃት፣ ህንጻዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም፣ በሰዎች ላይ፣ የሞት ወይም የመቁሰል አደጋ አልደረሰም፡፡

በአል ታንፍ ጦር ሰፈር የሚገኙት ዩናይትድ ስቴትስና የዓለም አቀፍ ወታደሮች፣ እስላማዊ መንግሥት ተዋጊዎቹን የሚከላከሉ የሶሪያ ተዋጊዎችን በማሰልጠን ላይ የሚገኙ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የጦር ሠፈሩ የሚገኝበት ቦታ አዋሳኝ ሲሆን የኢራቅ ባግዳድና የሶሪያ ደማስቆን የሚያገናኝና የዮርዳኖስ ኢራቅና ሶሪያ ድንበሮችን የሚገናኙበት አካባቢ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ኢራን መስመሩን እስከ ሜድትሬኒያን ድረስ በየብስ ለመገናኘት የምትጠቅምበት መንገድ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

XS
SM
MD
LG