በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አራት አገሮች ለሱዳን የሰላምና ዴሞክራሲ ጥሪ አቀረቡ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሳኡዲ አረብያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት እና እንግሊዝ ትናንት ረቡዕ ራቱ አገራት ለሱዳን ( QUAD for Sudan)በሚል ባወጡት የጋራ መግለጫ “ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊት ሱዳንን” እንደሚደግፉ አስታውቀዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጥቅምት 25 በሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አቡድል ፈታ አል ቡርሃን በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ሲቪሉ አስተዳደር መወገዱ ይታወቃል።

ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በወጣው በዚህ መግለጫ “ በሱዳን ባለው አሳሳቢ ሁኔታ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ስጋት እንጋራለን፡፡ የሲቪል መር የሽግግር መንግስትና ተቋማት በአስቸኳይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ቦታቸው እንዲመለሱም እንጠይቃለን” ብሏል፡፡

አራቱ አገሮች “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነስቶ በሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ንግግር እንዲጀመር ለሱዳን ህዝብ ሰላምና ደህንነት በቅድሚያ እንዲረጋገጥ” ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ አዛዥ ጀኔራል አቡድል ፈታ አል ቡርሃን፣ ወታደራዊ ግልበጣው የተካሄደው፣ የእርስ በርስ ጦርነቱን ለማስወገድ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ግልበጣው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ ወታደራዊ መንፈንቀል መንግስቱን የሚቃወሙ፣ የተለያዩ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ባላፈው ቅዳሜ በተካሄደው ሰልፍ ሶስት ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውና 38 የሚደርሱት መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልዑክ፣ ጀፍሪ ፊልትማን፣ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ የሱዳን ወታደሮች በቅዳሜው ሰልፈኞች ላይ የፈጸሙት ተግባር በአገሪቱ ስልጣን ወደ መጋራቱ ስምምነት የመመለስ አስፈላጊነትና እድልን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG