በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስሎቮኪያ ለዩክሬን ሚግ ተዋጊ ጀቶችን ልትሰጥ ነው


ስሎቮኪያ ለዩክሬን ሚግ ተዋጊ ጀቶችን ልትሰጥ ነው
ስሎቮኪያ ለዩክሬን ሚግ ተዋጊ ጀቶችን ልትሰጥ ነው

ስሎቮኪያ ለዩክሬን ሚግ ተዋጊ ጀቶችን ለዩክሬን የመስጠት እቅዷን ዛሬ ዓርብ አጸደቀች፡፡

ውሳኔው አገራቸው የሩሲያን ወረራ ለመመከት ለምታደርገው ጦርነት ይረዳል በሚል፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ለረጅም ጊዜ ሲጠይቋቸው ከነበሩት ጥያቄዎች መካከል አንዱን የመለሰ ነው ተብሏል፡፡

ስሎቮኪያ ከፖላንድ ቀጥሎ ለዩክሬን ሚግ ተዋጊ ጀቶችን በመስጠት ከኔቶ አባል አገሮች ሁለተኛዋ አገር መሆንዋ ተነግሯል፡፡

የስሎቮኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርድ ኼገር ያገለገሉ 13 ሚግ 29 ተዋጊ ጀቶችን ለዩክሬን በመስጠት አገራቸው ‘በትክክለኛው የታሪክ ገጽ” ላይ ትሆናለች ብለዋል፡፡

በሌላም በኩል የሩሲያ ወታደሮችና የግሉ ዋግነር ቡድን ጦር ከባክሙት ከተማ በስተ ምዕራብ ባክሙትካ ከተባለው ወንዝ አካባቢ ያለውን ስፍራ መቆጣጠራቸውን የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ማዕክል አስታውቋል፡፡

የተጠቀሰው ወንዝ በዶናባስ ግዛት የሚገኘው የባክሙት ከተማን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚደርገው ውጊያ የሚካሄድበት ግንባር እንደነበር መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል፡፡

የዩክሬን ኃይሎች በባክሙት በስተ ምዕራብ ያሉ አካባቢዎችን እየተከላከሉ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG