በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ባለሥልጣናት ከአውሮፓ መሪዎች ጋር ተሰበሰቡ


ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደ ሌይን
ዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደ ሌይን

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከአውሮፓው መሪዎች ጋር ዛሬ ዓርብ በአገሪቱ ዋና ከተማ ኪየቭ ተሰብሰበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አገራቸው የአውሮፓ ህብረት አባል አገር የምትሆንበትን ጊዜና በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች የሚጣሉበት ስብሰባ እንደሚሆን ተስፋ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ተንታኞች ምንም እንኳ ዩክሬን የህብረቱ አባል መሆኑን አጥብቃ የምትሻው ቢሆንም ወደዚያ ሚወስደው የተፋጠነ መንገድ ሊጨናገፍ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

ምንም እንኳ ህብረቱን በሩሲያው ወረራ ከጎና የቆመ ቢሆንም ስለህብረቱ አባልነት ግን እስካሁን ምንም ፍንጭ አላሳየም፡፡

ከዛሬው ስብሰባ በፊት ዜሌነስኪ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነር ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡

ዜሌንስኪ በየምሽቱ በሚያሰሙት የትናንት ሀሙስ ንግግራቸው፣ ቮን ደር ሌይን እና “ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያሉት ወዳጆቻችን በውህደት ጉዳና አገራችንን ህዝባችንን ለመከላከልና በመጠበቅ ላደረጉልን ተጨባጭ ድጋፍ” እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG